Back to Top
ነገር ግን የወር አበበ የሚያስቆም ኪኒን መውሰድ ጉዳት እንዳለው ከተረጋገጠ የሸሪያው ብይኔ ውን ምንድን ነው?
   ፊቅህ እና መሰረቶቹ        ፊቅህ (ኢስላማዊ ህግጋት)        ዒባዳዎች (አምልኳዊ ተግባራት)        ጦሃራ        የወር አበባ እና የወሊድ ደም

የወር አበበ የሚያስቆም ኪኒን መውሰድ ጉዳት እንዳለው ከተረጋገጠ በዚህን ጊዜ የሸሪዓው ብያኔ ምንድን ነው?


ጥያቄ(84): ነገር ግን የወር አበበ የሚያስቆም ኪኒን መውሰድ ጉዳት እንዳለው ከተረጋገጠ የሸሪያው ብይኔ ውን ምንድን ነው?
መልስ:

ጉዳት እንደሚያስከትል ከተረጋገጠ፡በሸሪዓ መርህ መሰረት እንደሚታወቀው ማንኛውም ጉዳት የሚያስከትል ነገር መጠቀም ለማንኛውም ሰው በሸሪዓው አይፈቀድለትም።ምክንያቱም አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላልና ፦

“ነፍሳችሁ አትግደሉ!አላህ በናንተ ላይ አዛኝ ነው።” [አኒሳእ: 29]

መልክተኛው(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ፦”ጁኑብ ሆነህ  ባልደረቦችህን አስገድክ?” ብለው ዐምር ኢብኑ አል ዐስ ሲጠይቁት ይህን አንቀፅ ማስረጃ በማድረግ መልሶላቸዋል። ብርዳማ ለሊት ላይ ጁኑብ ሆኖ ነበር እና ገላውን ሳይታጠብ ውዱ ብቻ(ተይሙም) አድርጎ ባልደረቦቹን አሰገደ።መልክተኛው ፦”ጁኑብ ሆነህ ባልደረቦችህን አስገድክ?” ብለው ሲጠይቁት፤ እሱም ቀጣዩን የቁርኣን አንቀፅ አስታወስኩ ፦ “ነፍሳችሁ አትግደሉ! አላህ በናንተ ላይ አዛኝ ነው።” [አኒሳእ: 29] ብሎ ሲመልሳላቸው ፈገግ አሉ።ይህን መረጃ ማድረጉን አረጋገጡለት። ማንኛውም በሰው ልጅ ላይ ጉዳት የሚያስከትል ነገር በሙሉ መጠቀም እንደማይችል ከዚህ መረዳት እንችላለን።




Share

ወቅታዊ