Back to Top

Logo Here

58/ትክክለኛው የተወሱል ዓይነትን እና ክፍሎቹን አውቀናል። ተቀባይነት የሌለውን የተወሱል ዓይነት ማወቅ የግል ይለናል፤ከንደገናም ክፍሎች ካሉት ቢጠቅሱልን።

ተቀባይነት የሌለውን የተወሱል ዓይነት፡ ተወሱል ባልሆነ ወይም በሸሪዓው በተወሱልነት ያልፀደቀ በሆነ ነገር ወደ አላህ ለመዳረስ ዱዓየማድረግ(የተወሱል) ክፍል ነው። ምክንያቱም በዚህ መልኩ ተወሱል ማድረግ ከንቱ፣ውድቅ እና ከአዕምሮና ከሸሪዓዊ መረጃዎች ጋር የሚጣረስ ተግባር ነው። ከዚህ ካልተፈቀደው  የተወሱል አይነት ፦ ሟችን በመጣራት ወደ አላህ ተወሱል ማድረግ ይገኝበታል። ማለትም ሟችን ወደ አላህ ዱዓ እንዲያደርግለት መማፀን፤ ይህ ትክክለኛ ሸሪዓዊ መዳረሻ አይደለምና። እንዲያውም አንድ ሰው ሟችን መጠየቁ ቂል መሆኑን  የሚጠቁም ነው።ምክንያቱም ሟች የሞተ እለት ስራው ተቋርጧልና ለማንም ዱዓ ማድረግ አይችልም። መልክተኛውም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንኳ ቢሆኑ ከሞቱ በኋላ ለማንም ዱዓ  ማድረግ አይችሉም።ለዚህም ሲባል ሰሓቦቹ ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ከሞቱ በኋላ አንዳቸውም በሳቸው ተወሱል አድርገው አያውቁም። በዑመር አገዛዝ ዘመን ሰዎች ድርቅ ደርሶባቸው ነበር። ዑመር፦ “አላህ ሆይ! በነቢያችን (ዱዓ) ተወሱል እንዳርግ ነበር ዝናብንም ታጠጣን ነበር። አሁን ደግሞ በዓባስ ረዲየላሁ ዐንሁ ዱዓ ተወሱል እንዳርጋለንና ዝናብን አዝንብልን።” ከሟች ዱዓ እንዲያደርግ መከጀል ተቀባይነት ቢኖረው እና ትክክለኛ መዳረሻ ቢሆን ዑመርና አብረውት የነበሩት ሰሓቦቹ ከነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ዱዓን በከጀሉ ነበር። ምክንያቱም ከዓባስ ዱዓ  የመልክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ዱዓ ይበልጥ ተቀባይነት እንዳለው ምንም ጥርጥር የለውም። ያም ሆነ ይህ! ከሟች ዱዓ በመከጀል ወደ አላህ ተወሱል ማድረግ ባጢል የሆነ የማይፈቀደ የማይቻል የተወሱል ዓይነት ነው።

ትክክለኛ ካልሆነው የተወሱል ዓይነት የሚመደበው፦ በነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ክብር ተወሱል ማድረግ ይገኝበታል። ለምሳሌ ፦ አላህ ሆይ! በነቢዩ ክብር ይሁንብህ እንዲህ አድርግልኝ። ብሎ መማፀን ለአብነት ተጠቃሽ ነው። ምክንያቱም የነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም )  ክብር ለርሳቸው እንጂ ለአንተ ምንም አይጠቅምህም። ለአንተ የሚጠቅመው በአላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ)  ተወሱል ማድረግህ ብቻ ነው። ከዚህ በፊት እንዳልነው ፦ ጥሩ እና ፍርያም የሆነ መዳረሻና ጥረት መውሰድ ተወሱል ይባላል። መልክተኛው አላህ ዘንድ ክብር ያላቸው መሆኑ ምን ፋይዳ አለው?! ስለዚህም ትክክለኛው ወደ አላህ የሚያዳርስህ ተወሱል ማድረግ የምትሻ  ከሆነ፤ አላህ ሆይ! መልክተኛውን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እውነተኛ ናቸው ብዬ በማመኔ ይሁንብህ። አሊያም ረሱሉን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) በመውደዴ ይሁንብህ። እና የመሳሰሉትን በማለት ዱዓ ማድረግ ይቻላል። ይህ ትክክለኛውና ጠቃሚ የተወሱል ዓይነት ነው።