ጥያቄ(99): አንዳንድ ሰዎች ኢቃም ካለ በኋላ ይመጡና ኢማምን ተከትሎ መስገድ ከጀመሩ በኋላ ስንት ረከዓ እንዳመለጣቸው ይዘነጋሉ። ከዚያም አጠገባቸውና አብሯቸው ሰላት የጀመረ ሰውን ተከትለው ይሰግዳሉ። ይህ በሸሪዓው እንዴት ይታያል?
መልስ:
እንዳልከው ይህ ክስተት ብዙ ጊዜ ይከሰታል። ሁለት ሰዎች አብረው ሰላት ውስጥ ከገቡ በኋላ አንደኛው ስንት ረከዓ እንደሰገደ ይረሳል። ከዚያም ከጎኑ ያለውን ሰው ተከትሎ ይሰግዳል። ከጎኑ ያለው ሰው ላይ ያለው ግምት ወይም እርግጠኝነት እስካልተቃረነ ድረስ ተከትሎ መስገድ ችግር የለውም እንላለን። ምክንያቱም ይህ ተግባር እርግጠኛ ወደሆንበት ነገር እንደመመለስ ስለሚቆጠር። ዒባዳን አስመልክቶ ከኡለማዎች ንግግር ሚዛን የሚደፋው አቋም እርግጠኛ ወደሆንበት ነገር መመለስ ችግር የለውም የሚለው ነው።