ጥያቄ(97): ከነዚህ ማዕዘናት አንዱን የተወ በሸሪዓው የሚሰጠው ሁክም ምንድ ነው?
መልስ:
ከነዚህ ማዕዘናት አንዱን እያወቀ በመተዉ ብቻ ሰላቱ ተቀባይነት የለውም። ሆኖም ረስቶ ከሆነ የተወዉን ማእዘን መመለስ ወይም ማስገኘት ይኖርበታል። እንበልና ሩኩዕ ማድረግ ቢረሳ ፋቲሓን አንብቦ ከጨረሰ ሩኩዕ ሳያደርግ ሱጁድ ቢያደርግ ከዚያም ሱጁድ ላይ ሳለ ሩኩዕ አለማድረጉን ቢያስታውስ፤ዳግም በመቆም ሩኩዕ ማድረግ ከዚያም ሰላቱን በተሟላ መልኩ መስገድ ግዴታ ይሆንበታል። ወደ ሁለተኛው ረከዓ ጋር ካልተቀጠለ ወደ ረሳው የሰላት ማዕዘን በመመለስ መስገድ ይጠበቅበታል። ነገር ግን ሁለተኛው ረከዓ ላይ ከደረሰ ሁለተኛው ረከዓ እንደ መጀመሪያው ይቆጠራል።
ማለትም አንድ ሰጋጅ ሩኩዕ ሳያደርግ ሱጁድ አደረገ ከዚያም በሁለት ሱጁዶች መካከል ያለውን መቀመጥ ቢቀመጥ ቀጥሎም ዳግም ሱጁድ አደረገ፤ ከዚያም ሩኩዕ አለማድረጉን ካስታወሰ ወደ ቂያም በመነሳት ሩኩዕ ማድረግ ይኖርበታል። ከዚያም የተቀረውን ሰላት አሟልቶ ይሰግዳል። ሆኖም ወደ ሁለተኛው ሩኩዕ ከተሸጋገረ በኋላ ሩኩዕ አለማድረጉን ካስታወሰ ይህኛው ረከዓ የመጀመሪያው ረከዓ ማለትም ሩኩዕን የረሳበት ረከዓን ይተካል።
እንደዚሁም ሁለተኛውን ሱጁድ ማድረግ ቢረሳ አንደኛውን ሱጁድ አድርጎ ወደ ቂያም ብድግ ብሎ ቁርኣን እየቀራ ሳለ ሁለተኛው ሱጁድ መርሳቱ ትዝ ቢለው፤ እንዲሁም በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ሳይቀመጥ ሱጁድ ቢያደርግ በዚህን ግዜ ወደኋላ በመለስ በሁለቱ ሱጁዶች መካከል መቀመጥ ይኖርበታል። ከዚያም ሁለተኛውን ሱጁድ ያደርጋል። ቀጥሎም ሰላቱን ቅደም ተከተሉን ጠብቆ በተሟላ መልኩ ይሰግዳል። ሁለተኛው ሱጁድ እና በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ያለውን መቀመጥ ረስቶ ሩኩዕ ካደረገ በኋላ ቢያስታውስ ሱጁድ ማድረግ እና በሁለቱ ሱጁዶች መካከል መቀመጥ ይኖርበታል። ከዚያም ሰላቱን ይቀጥላል። ነገር ግን ሁለተኛው ሱጁድ እና በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ያለውን መቀመጥ ረስቶ ሁለተኛው ረከዓ ላይ ሱጁድ ሲያደርግ ትዝ ቢለው ይህኛው ማለትም የመጀመሪያውን ረከዓ እንዳልሰገደ በመቁጠር ሁለተኛው ረከዓ እንደመጀመሪያው ረከዓ ይቆጠርለታል።
ተጨማሪ የሰላት ተግባሮች በመጨመራቸው የተነሳ በሁሉም ሁኔታዎች ላይ ማለትም ካላይ በጠቀስናቸው የመርሳት ዓይነቶች ላይ ሰላቱን ካገባደደ በኋ ሱጁድ ሰህው (የመርሳት ሱጁድ) ማድረግ ይኖርበታል። ምክንያቱም የመልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሱናዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ፤ሰላት ውስጥ ጭማሪ ተግባሮች ከተፈፀሙ ከሰላት በኋላ ሱጁድ መደረግ ይኖርበታል።