Back to Top
አንዲት ሴት ሐጅ ስነ ስርዓት ላይ ሳለች ሀጇን  በአግባቡ መፈፀም ያስችላት ዘንድ  የወር አበባ ደም የሚያስቆም ኪኒን መውሰድ ትችላለችን?
       ፊቅህ (ኢስላማዊ ህግጋት)        ዒባዳዎች (አምልኳዊ ተግባራት)        ጦሃራ        የወር አበባ እና የወሊድ ደም

በሐጅ ወቅት የወር አበባ ደምን የሚያስቆም ኪኒን መውሰድ በሸሪዓው ያለው ብያኔ


ጥያቄ(83): አንዲት ሴት ሐጅ ስነ ስርዓት ላይ ሳለች ሀጇን  በአግባቡ መፈፀም ያስችላት ዘንድ  የወር አበባ ደም የሚያስቆም ኪኒን መውሰድ ትችላለችን?
መልስ:

በመሰረቱ በዚህ ላይ በሸሪዓው ያለው ብያኔ  ይቻላል የሚል ነው። አንዲት ሴት ባሏ  ከፈቀደላት የወር አበባ የሚያስቆም ኪኒን መወሰድ ትችላለች የሚለው ነው። ነገር ግን ይህን ኪኒን መውሰድ ማህፀን፣ ጅማት እና  ደም ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል ከአንዳንድ ሐኪሞች የደረሰኝ መረጃ አለ። እንዲያውም አንዳንድ ሀኪሞች ድንግል የሆነች ሴት ይህን ኪኒን ከወሰደች እስከ ማህንነት ያደርሳታል ብለው ነግረውኛል። በዚህም የተነሳ ሴቷ መሀን ትሆናለች።ይህ ደግሞ  እጅግ ከፍተኛ አደጋ  ነው። አንዳንድ ሐኪሞ ች ያሉት ነገር ከእውነት የራቀ  አይደለም። ምክንያቱም የወር አበባ ደም ማለት ተፈጥሯዊ ደም ነውና ሰዎች በነዚህ መድሃኒቶች አማካኝነት ለማስቆም ሙከራ  ሲያደርግ ተፈጥሮ ን ለመፃረር ሞክሯል፤ ተፈጥሮ ን መቃረን አካል ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል ምንም ጥርጥር የለውም። ምክንያቱም ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ መውጣት ባለበት ሰዓት ተገድቦ እንዳይወጣ ማእቀብ ይደረግበታል ማለት ነው። ስለሆነም ይህን ዓይነቱ ኪኒን ረመዳንም ይሁን አይሁን እንዳይወስዱ ስል ሴቶቻችን  እመክራለሁ። ነገር ግን ዑምራና  ሐጅን አስመልክቶ ግን ምንባትም ወሳኝና  እጅግ አስፈላጊ ሆኖ ስለሚገኝ እንዲሁም ወቅቱም አጭር ጊዜ  በመሆኑ የተነሳ መጠቀሙ ችግር የለውም። ምናልባትም ሴቷ እድሜ ልኳን የዑምራን እድል ላታገኝ ስለምትችል እዚህ ቦታ ላይ መጠቀሙ ችግርም ሆነ ጉዳት የለውም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።  




Share

ወቅታዊ