ጥያቄ(76): በቀዳዳ ካልሲ ወይም ኹፍ ላይ ፣አሊያም ስስ ካልስ ላይ ማበስ ይቻላልን?
መልስ:
እዚህ ላይ ሚዛን የሚደፋው አቋም እነዚህ ጥያቄው ላይ የተጠቀሱት ነገሮች ላይ ማበስ ይቻላል የሚለው ነው። ማለትም ቀዳዳ እና ስስ ካልሲ ከካልሲው በስተጀርባ የሰውነት ቆዳ ቀለም ቢታይም እንኳ ላዩ ላይ ማበስ ይቻላል። ምክንያቱም ኹፍ ላይ ለማበስ የእግርን ክፍል መሸፈን መስፈርት አይደለም። እግር መሸፈን የሚያስፈልገው የሀፍረት አካል አይደለምና። ኹፍ ላይ ማበስ የተፈቀደበት ዓላማ ውዱእ ማድረግ በፈለገ ቁጥር ኹፍን ወይም ካልሲን በማውለቅ እንዳይቸገር ሰዎች ላይ ማግራራትና ማቅለል ተፈልጎ ነው። እንዲያውም እንዲህ አይነት ካልሲ ወይም ኹፍ የለበሰን ማበስ ትችላለህ እንለዋለን። በሸሪዓው ኹፍ ላይ ማበስ የተፈቀደበት ምክንያትና ዓላማ ይኸው ነው። ይህ ኹፍ የተፈቀደበት ምክንያት ካስተዋልክ ኹፍ ወይም ካልሲው ቀዳዳም ይሁን ያልተቀደደ፣ ስስም ይሁን ወፍራም ሁሉም እኩል መሆኑ ትመለከታለህ።