ጥያቄ(75): ነገር ግን ካልሲ ወይም ኹፍ ላይ ለማበስ ካልሲ ወይም ኹፍ ላይ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ይኖራሉን?
መልስ:
ምንም መስፈርት የለውም።ምናልባት ካልሲው ወይም ኹፉ ጠሃራ መሆን አለበት የሚለው ሊሆን ይችላል። ነጃሳ ከሆነ ላዩ ላይ ማበስ አይቻልም። አንድ ሰው ከነጃሳ የሆነ ቆዳ የተሰራ ኹፍ ቢጠቀም ለምሳሌ የውሻ እና የአውሬ ቆዳ ኹፍ አድርጎ ቢጠቀም፤ላዩ ላይ ማበስ የተከለከለ ነው። ምክንያቱም ነጃሳ ነውና። ነጃሳን ተሸክሞ ሰላት መስገድ አይቻልም። ነጃሳ ላይ ማበስ ይባስ መበከልን እንጂ ሌላን አይጨምርም።