Back to Top
የጣሃራ መሰረት የሆነው ማለትም ውሃ ሳይኖር ሲቀር ውሃን የሚተካ ነገር ምንድ ነው?

ጥያቄ(66): የጣሃራ መሰረት የሆነው ማለትም ውሃ ሳይኖር ሲቀር ውሃን የሚተካ ነገር ምንድ ነው?
መልስ:

ውሃን የሚተካ አፈር ነው። ውሃ ሳይኖር አሊያም መጠቀሙ ሰውነት ላይ አደጋ የሚያስከትል ከሆነ ውሃ መጠቀም በመተው አፈርን ይጠቀማል፤ ማለትም ተየሙም ያደርጋል። ይኸውም ተየሙም የሚያደርገው ሰው መዳፎቹን ከመሬት ላይኛውን ክፍል በመምታት በመዳፎቹ ፊቱን ያብሳል ቀጥሎም መዳፎች እርሰ በርሱ ያብሳቸዋል። ነገር ግን ይህ ጠሃራ ሐደስ ላይ ብቻ ነው። ከኹብስ (ነጃሳ) ጠሃር የሚሆነው ተየሙም  ይተካውም። አካል ላይ ወይም ልብስ ላይ አሊያም ቦታ ላይ ነጃሳ ካለ በተየሙም ሊወገድ አይችልም። ምክንያቱም ከኹብስ (ነጃሳ)  ጠሃራ ሲደረግ ከላይ በዓይን የሚታየው ነጃሳ ማስወገድ ተፈላጊ ነው። እዚህ ቦታ ላይ ለኢባዳ ብቻ ብሎ(ነይቶ) መስራት መስፈር አይደለምና።  ለዚህም ሲባል ሰውዬው ሳያስበው የሚታየው ነጃሳ ቢወገድ ቦታው ጡሃራ ነው እንላለን። ለምሳሌ ሰውዬው ሳያያው ወይም ሳያውቀው ነጃሳ የሆነው ቦታ ላይ ወይም ልብስ ላይ ዝናብ ዘንቦ ከነጃሳ ቢያፀዳው ጠሃራ ይሆናል። ነገር ግን ከሀደስ ጠሃራ መሆን ግን ፈፅሞ የተለየ ነው። ከሐደስ ጠሃራ ማድረግ ዒባዳ ነውና ኒያ እና እያወቁ መፈፀም መስፈርት ነው።




Share

ወቅታዊ