ጥያቄ(65): ጠሃራ የሚገኝበት መሰረት ምንድ ነው?
መልስ:
ሐደስን አስመልክቶ ጠሃራ የሚገኝበት መሰረት ውሃ ነው። ውሃው ንፁህም ይሁን በጠሃራ ነገሮች የተቀየረም ይሁን በውሃ ካልሆነ ጠሃራ ሊገኝ አይችልም። ምክንያቱም ውሃ በጠሃራ ነገሮች ከተቀየረ ውሃ የሚለው ስም ላይ ፀንቶ ይቆያል፣ጠሃራነቱ አይወገድም፣ በራሱ ጠሃራና ሌላውንም ጠሃራ ማድረግ ይችላል የሚለው አባባል ሚዛን የሚደፋ አባባል ነው።
ውሃ ከሌለ አሊያም ውሃ መጠቀም ሰውነት ላይ አደጋ የሚያስከትል ከሆነ ውሃ በመጠቀም ፈንታ በአፈር ተየሙም ይደረጋል። በመዳፎች መሬትን በመታት ፊቶችን ያብሳል እና መዳፎችን እርሰ በርሳቸው ያብሳቸዋል። ይህ የሐደስ ጠሃራ አስመልክቶ ሲሆን የኹብስ(ነጃሳ) ጠሃራ ደግሞ በውሃም ሆነ ማንኛውም ነጃሳን በሚያስወግዱ ነገሮች ጠሃራ ሊገኝ ይችላል። በውሃ ወይም በቤንዚን ወይም በሌሎች ፈሳሽ ወይም ደረቅ እጥበት እና ማስወገጃዎች ሙሉ ለሙሉ ከላይ በዓይን የሚታየው የነጃሳ አይነት ከተወገደ ከኹብስ ጠሃራው በዚሁ መልኩ ተገኘ ማለት ነው። ከዚህም ማብራሪያ በመነሳት ኹብስ የሆኑ ነጃሳዎች እንዴት እንደሚወገዱና ሐደስ ላይ ጠሃራ እንዴት እንደሚከሰት በሁለት መካከል ያለው ልዩነት ግልፅ ይሆንልናል ማለት ነው።