ጥያቄ(64): ጠሃራ ማለት ምን ማለት ነው?
መልስ:
ጠሃራ ማለት በቋንቋ ደረጃ መፀዳዳት መጥራት ማለት ነው።በሸሪዓዊ ትርጓሜው ደግሞ ሁለት አይነት ነው። መንፈሳዊ ጠሃራ(ንፅህና) እና አካላዊ ጠሃራ(ንፅህና) ናቸው። መንፈሳዊ ንፅህና ማለት አምልኮትን ከሽርክ፣ከቢድዓ ማጥራት፣ከሙስሊሞች መካከል ይህ ለነሱ ከማይገባቸው ጥላቻ፣ከምቀኝነት፣ ከቂም በቀል እና ከመሳሰሉት ባህሪያት ልብን ማፅዳት ማለት ነው።
ሐሲያዊ ንፅህና ማለት ደግሞ አካልን ማፅዳት ማለት ሲሆን ሁለት አይነት ነው። አንደኛው ሰላት እና ጠሃራ መስፈርት የሚደረግላቸው መሰል ዒባዳዎችን እንዳይፈፀሙ የሚከለክሉ ነገሮችን እና ቆሻሻ ወይም ነጃሳማስወገድ ማለት ነው።
በመጀመሪያ መንፈሳዊ ስለሆነው ጠሃራ እንነጋገር፤ የአላህ መብት አስመልክቶ ከሽርክና ከቢድዓ ልብን ማፅዳት ማለት ሲሆን ከሁለቱ የጠሃራ አይነት እጅጉ የላቀው ነው። ለዚህም ሲባል ሁሉም የኢባዳ አይነቶች እዚህኛው ጠሃራ ላይ የሚገነቡ ናቸው። ማንኛውም ሰው በሽርክ የተለወሰ ሰው ኢባዳው ተቀባይነት አያገኝም። ማንኛውም ሰው ወደ አላህ የሚቃረብበት ቢድዓ ተቀባይነት የለውም። አላህ ያልደነገገው ነውና። አላህ እንዲህ ይላል፦
መልዕክተኛውም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) “የእኛ ትእዛዝ የሌለበት ተግባር ተቀባይነት የለውም” ብለዋል።
ከዚህም በመነሳት ትልቁን የሽርክ አይነት የፈፀመ ዒባዳው ተቀባይነት የለውም። ቢሰግድ፣ቢፆም፣ቢለግስም ሐጅ ቢያደርግም። ከአላህ ውጭ የሚጣራ ወይም የሚያመልክ አምልኮቱ ተቀባይነት የለውም። በአምልኮቱ ጥርት አድርጎ አላህን ቢገዛም እንኳ በሌላ በኩል ሽርክን እስከሰራ ኢባዳው ተቀባይነት አይኖረውም።
ለዚህም ሲባል አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ) ሙሽሪኮችን ነጃሳ ሲል ይገልጻቸዋል። አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ) እንዲህ ይላል፦
መልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) አማኞች ነጃሳ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። መልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲህ ብለዋል፦ “ሙእሚን አይነጀስም።” ይህ እንግዲህ አንድ አማኝ ቀልቡ ከዚህ የሽርክ አይነት ይጠራ ዘንድ ከባድ የሆነ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ እንረዳለን።
እንደዚሁም ደግሞ አንድ አማኝ አማኞችን ከመጥላት፣ከቂም፣ከምቀኝነት፤ ሙዕሚኖችን ከመጥላትና ከመሳሰሉት ልቡን ሊያጠራ ይገባል። እነዚህ ባህሪያት እጅግ የተወገዙና የአንድ አማኝ ባህሪያት አይደሉም። አንድ አማኝ ለሌላው አማኝ ወንድም ነው። ሊጠላውና ወሰን ሊያልፍበት እና ሊመቃኘው አይገባም። እንዲያውም ለርሱ መልካም እንደሚፈልገው ሁሉ ለወንድሙም መፈለግ ይኖርበታል። መልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) አንድ አማኝ ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ኢማን የለውም እስከማለት ደርሰዋል። መልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲህ ብለዋል፦ “ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ ካልወደደ ከእናንተ አንዳችሁም እምነቱ የሞላ አይደለም።” ብዙ የመልካምና የሰናይ ተግባራት፣የተቅዋ የዙህድ ፈጻሚዎች መስጊድን የሚመላለሱና መስጂድን በቂርኣት በዚክር እና በሰላት ሊገነቡ ይችላሉ ሆኖም ለሙስሊም ወንድሞቻቸው ጥላቻ እና አላህ ለለገሳቸው ጸጋዎች ቀልባቸው ውስጥ ምቀኝነት ያኖራሉ። ይህ ተግባራቸው ብዙ የሚሰሯቸው ኢባዳዎች ላይ ክፍተት ይፈጥርባቸዋል። ሙስሊም ወንድሞችን አስመልክቶ ሁላችንም ከዚህ ነጃሳ ባህሪያት ቀልባችን ልናጠራ ይገባል።
ሒሲይ(አካላዊ) ጠሃራ ደግሞ እንዳሳለፍነው ሁለት አይነት ነው። ጠሃራ መስፈርት የሚደረግላቸው ኢባዳዎችን እንዳይፈፀሙ የሚያደርገውን ነገር እና ርክሰትን ማስወገድ ማለት ነው።
አንደኛው፦ አካል ላይ ያለ ርክሰትን ማስወገድ ሲባል ፤ ትንሹና ትልቁ ሐደስ(ርክሰት) ማስወገድ ማለት ነው። ትንሹ ሐደስ የሚወገደው አራት የሰውነት አካሎችን በውሃ በማጠብሲሆን በትልቁ ሐደስ ደግሞ ሙሉን ገላ ማጠብ ነው። ይህን በማስመልከት አላህ(ሱ.ወ.) ቀጣዩ ን አንቀፅ አውርዷል።
ሁለተኛው፦ የጠሃራ አይነት ከኹብስ ( ከነጃሳ) መፀዳዳት ሲሆን አላህ(ሱብሃነሁ ወተዐላ) በባሮች ላይ እንዲጥራሩና እንዲፀዳዱ ግዴታ ያደረገባቸው ነገሮች ናቸው።ለምሳሌ ሽንትና ሰገራ እና የመሳሰሉት እንዲሁም ባጠቃላይ በሐዲስ እና በሸሪዓው ነጃሳ መሆናቸው ተጠቁመው የመጡ ነገሮችን በሙሉ ያካትታል። ለዚህም ሲባል ፉቃሃዎች (የፊቅህ ሊቃውንት) አላህይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፦ ጠሃራ የሚኮነው ወይ ከሐደስ ወይ ደግሞ ከኹብስ(ነጃሳ) ነው። ይህ ማለትም ከኹብስ (ነጃሳ) ጠሃራ መሆንን አስመልክቶ ከሱነን ባለቤቶች ተዘግቦ የመጣው ሐዲስ ከኹብስ (ነጃሳ) ጠሃራ መሆን ግዴታ መሆኑን ይጠቁማል። መልክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ከእለታት አንድ ቀን ሰሓቦችን እያሰገዱ ጫማቸውን አውልቀው ጣሉ ሰሓቦችም ጫማቸውን አውልቀው ጣሉ። መልክተኛውም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ሰላታቸውን እንዳጠናቀቁ ሰሃቦች ለምን ጫማቸውን እንዳወለቁ ሲጠይቋቸው እነርሱም” ጫማዎትን ሲያወልቁ ተመለከትን እኛም አወለቅን።” አሏቸው መልክተኛውም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) “ጂብሪል መጥቶ ጫማዬ ላይ ነጃሳ እንዳለ ነገሮኝ ነው።” በማለት ነገሯቸው። ይህ የጠሃራ ምንነት አስመልክቶ ሊባል የሚችል ጥቅላዊ ንግግር ነው።