ጥያቄ(6): ተውሒድ ማለት ምንማለት ነው?
መልስ:
ተውሂድ ማለት ”ወሐደ” አንድ አደረገ፤ “ዩወሒዱ” አንድ ያደርጋል፤ ከሚለው የአረብኛ ስረውቃል የመነጨ ነው። ይህም ማለት አንድ ነገርን አንድ ማድረግ ማለት ሲሆን ይህ የሚረጋገጠው ”ኢስባት” በማጽደቅና “ነፍይ” ውድቅ በማድረግ ነው።
አንድ ተደርጎ ከተነጠለው አካል ውጭ ፍርድን ውድቅ ማድረግ። ስለዚህም አምልኮትን ከአላህ ውጭ ካሉ አማልክት ውድቅ አድርጎ ለአላህ ብቻ ማጽደቅ ይገባል። የሰው ልጅ ላ ኢላህ ኢለላህ ብሎ በመመስከር አምልኮትን ከአላህ ውጭ ካሉ አማልክት ውድቅ በማድረግ ለአላህ ብቻ ካላፀደቀ ተውሒዱ የተሟላ አይሆንም። ያለ ማፅደቅ ውድቅ ማድረግ ይህ ማራቆት ይባላል። ውድቅ ሳያደርጉ ማጽደቅ ብቻውን ሌላውን አካል እንዳያጋራ አይከለክልም።
ለምሳሌ ፦ እገሌ ቆሟል ብለህ ብትናገር ሰውዬው መቆሙ አረጋገጥክ ማለት ነው። ነገር ግን መቆም በሚባለው ድርጊት እርሱን ብቻ አልነጠልከውም። ምክንያቱም ሌላውም አካል በዚህ ድርጊት ሊጋራው ይችላልና። “አልቆመም” ብለህ ብትናገር ደግሞ መቆም የሚባለውን ድርጊት ከሁሉም ውድቅ አደርግክ። በዚህም የተነሳ ለአንድም አካል መቆምን አላፀደቅክም ማለት ነው። ነገርግን ዘይድ እንጂ ማንም አልቆመም ስትል ዘይድ መቆም በሚባለው ድርጊት ነጥለሀዋል ማለት ነው። ከርሱ ውጭ ያሉ አካሎችን መቆም በሚባለው ድርጊት ውድቅ ስላደረግክ።
ተውሒድን በተጨባጭ ማረጋገጥ ማለት ይህ ነው። ማለትም ተውሒድ ተውሒድ የሚሰኘው “ኢስባት” ማጽደቅና “ነፍይ”(ውድቅ) ማድረግን በውስጡ ሲያካትት ብቻ ነው ።