Back to Top
የሽርክ ክፍሎች ምን ምን ናቸው?

ጥያቄ(45): የሽርክ ክፍሎች ምን ምን ናቸው?
መልስ:

ከዚህ በፊት እንዳሳለፍነው ተውሒድ በውስጡ ነፍይና ኢስባትን ያካትታል። በነፍይ ላይ ብቻ መገደብ መልዕክቱን ትርጉም አልባ እንደማድረግ ይቆጠራል። በኢስባት ላይ ብቻ መገደብ ደግሞ አምልኮትን ሌላው እንዳይጋራ አይከለክልም። ስለዚህም ተውሒድ ላይ ኢስባትና ነፍይን ማካተት የግድ ነው። በዚህ መልክ በሐቁ ያላፀደቀ በአላህ ላይ አጋርቷል።

ሽርክ ሁለት አይነት ነው።

አንደኛው የሽርክ አይነት፦ትልቁ ሽርክ- ይህ ከኢስላም የሚያስወጣ ነው። ትልቁ ሽርክ ማለት በሸሪዓ መልዕክቶች ላይ ሽርክ በሚል ከምንም ነገር ጋር ሳይያያዝ በልቁ የመጣ እና የፈፀመው ሰው ከእስልምና ይወጣል የሚል መልክት በውስጡ የያዝ ነው። ለምሳሌ ፦ ከአምልኮ ዘርፎች አንዱን ከአላህ ውጭ ላለ አካል አሳልፎ መስጠት የመሰለ ተግባር፤ ከአላህ ውጭ ላለ አካል መስገድ ፤ ወይም ከአላህ ውጭ ላለ አካል እርድን መፈፀም፤ ከአላህ ውጭ ያለ አካልን መጣራት ከትልቁ ሽርክ የሚመደብ ነው።

ለምሳሌ ፦ የሞተን አካል የተቀበረን ሰው መጣራት፤ አላህ እንጂ ሊሰጠው የማይችል ነገርን ከአላህ ውጭ ያለ እና አጠገቡ የሌለን አካል መጣራት የመሳሰሉት ትልቁ ሽርክ ናቸው። የእውቀት ባለቤቶች ሽርክን አስመልክቶ በፃፉት መሰረት የሽርክ አይነቶች ይታወቃሉ።

ሁለተኛው የሽርክ አይነት፡ ትንሹ ሽርክ ሲሆን ማንኛውም ንግግር ወይም ተግባር በሸሪዓ መልዕክቶች ላይ ሽርክ በሚል ከምንም ነገር ጋር ሳይያያዝ በልቁ የመጣ ሲሆን ፤ነገር ግን የፈፀመው ሰው ከእስልምና አይወጣም። ለምሳሌ ከአላህ ውጭ ባለ ነገር መማል። የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم ) እንዲህ ብለዋል፦ “ከአላህ ውጭ ባለ  ነገር የማለ በእርግጥ ከፍሯል ወይም አሻርኳል።” ነገር ግን ከአላህ ውጭ ባለ ነገር ሲምል የሚምልበት አካል እንደ አላህ ሀያል ነው ብሎ ያመነ መሆን የለበትም። ይህ ከሆነ ብቻ ነው ትንሹ ሽርክ የምንለው። ይህ የሚባልበት ግለሰብ የሚከበር ወይም የማይከበር ሊሆን ይችላል። በነቢዩ እንኳ መማል አይፈቀድም። በመሪም ሆነ በባለስልጣን በከዕባም በጂብሪልም ሆነ በሚካኤል እና በመሳሰሉት መማል አይቻልም። ምክንያቱም ሽርክ ነውና። ነገርግን ትንሹ ሽርክ ሲሆን ከእስልምና አያስወጣም።

ከትንሹ ሽርክ መካከል፦ ቀለል ያለው ይይሉኝ፤ ምሳሌ አንድ ሰው ለአላህ ብሎ እየሰገደ ሳለ ሰዎች እንደሚመለከቱት ሲያውቅ ለይይዩልኝ ብሎ ሰላቱ ቢያሳምር ይህ ትንሹ ሽርክ ይባላል። ስራው (ኢባዳው) ለአላህ ቢሆንም ሰዎች እንዲያዩለት ብሎ ኢባዳውን ማስዋብ የሚባለው ነገር ገብቶበታል። እንደዚሁም ወደ አላህ ለመቃረብ ብሎ ገንዘቡን ወጪ ቢያደርግ ነገር ግን በዚህ ተግባሩ ሰዎች እንዲያወድሱት ቢፈልግበት ይህም ትንሹ ሽርክ ላይ ወድቋል። በተጨማሪም የእውቀት ባለቤቶች ሽርክን አስመልክቶ በፃፉት መፅሃፋቸው ላይ የትንሹ ሽርክ አይነቶች በዝርዝር ይታወቃሉ።




Share

ወቅታዊ