Back to Top
መልክተኛው ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ላይ ድግምት እንደተሰራባቸው የሚገልፁ ዘገባዎች መጥተዋል፤ ስለዚህም ነቢዩ ላይ ድግምቱ እንዴት እንደነበረ እንዲነግሩን እንሻለን። በተጨማሪም እሳቸው ላይ ድግምት መደረጉ ከነብይነት ማዕረግ ጋር የሚቃረን ነገር ነውን?

ጥያቄ(43): መልክተኛው ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ላይ ድግምት እንደተሰራባቸው የሚገልፁ ዘገባዎች መጥተዋል፤ ስለዚህም ነቢዩ ላይ ድግምቱ እንዴት እንደነበረ እንዲነግሩን እንሻለን። በተጨማሪም እሳቸው ላይ ድግምት መደረጉ ከነብይነት ማዕረግ ጋር የሚቃረን ነገር ነውን?
መልስ:

በቡኻሪና ሙስሊም እንዲሁም ሌሎች እንደዘገቡት መልዕክተኛው (ሰለለሁ አለይሂ ወሰለም) ድግምት ተሰርቶባቸዋል።ነገር ግን ድግምቱ ከድንጋጌና  ከወህይ አንፃር ምንም ተፅእኖ አልነበረውም። የድግምቱ ውጤት የመጨረሻው በርሳቸው ላይ ሊያደርስ የቻለው ነገር ቢኖር አንድን ነገር ሳያደርጉት ያደረጉ ይመስላቸው ነበር። ይኸኛውን ድግምት የሰራባቸው ግለሰብ ለቢድ ኢብኑ አዕሰም በመባል የሚጠራ የሁዲ ነበር። ድግምቱን በነቢዩ ላይ ቢሰራም አላህ ከድግምቱ ሴራ ነፃ አወጣቸው። ይህን አስመልክቶ ወሕይ መጣላቸው። በ“ሙዐዊዘተይን” (ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ እና ቁል አዑዙ ቢረቢ ፈለቅ) ጥበቃ ተደረገላቸው።

ይህ አይነቱ ድግምት ነብይነታቸው ላይ ምንም አይነት ተፅእኖ የለውም። ምክንያቱም ከላይ እንዳሳለፍነው በወሕይና በሚሰሯቸው አምልኮት ላይ ሲሕሩ ምንም አይነት ተፅእኖ አልነበረውም። አንዳንድ ሰዎች ነቢዩ e ላይ ሲሕር ተሰራ የሚለውን አስተባብለዋል። ምክንያቱም   ካፊሮች ወይም በዳዮቹ፦

“የተደገመበትን ሰው እንጂ አትከተሉም።” [አልኢስራእ:47]

ብለው የተናገሩትን ቃል ማረጋገጥ ሊሆንብን ነው ማለት ነው! የሚል ምክንያት ያቀርባሉ። ነገር ግን እነዚህ በዳዮች ወይም ከሃዲያን መልክተኛውን ከገለፁበት ባህሪ ጋር መስማማት ያስጨብጣል ከሚለው ሀሳብ ጋር ያለምንም በፍፁም አያስኬድም። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች የሚሉት ነቢዩ e ወህይ መጥቶላቸው የሚናገሩትን በሙሉ ከድግምት የተነሳ አዕምሮ  ስለታወከ የሚዘባርቀው ወሬ ነው የሚሉት። ነገር ግን መልክተኛው ላይ ተከስቶ የነበረው የድግምት አይነት ወሕይም ላይ ሆነ አምልኮታቸው ላይ ተፅእኖ አልነበረውም። በትክክለኛ ዘገባ የመጡ መረጃዎችን በእኛ የተሳሳተ አረዳድ የተነሳ ዘገባዎችን ልናስተባል አይገባም።




Share

ወቅታዊ