Back to Top
በፍጡሮች ላይ የመጀመሪያው ግዴታ ምንድን ነው?

ጥያቄ(4): በፍጡሮች ላይ የመጀመሪያው ግዴታ ምንድን ነው?
መልስ:

የመጀመሪያው ግዴታ ነገር ሰዎች በቅድሚያ ጥሪ የሚደረግላቸው ነገር ሲሆን መልክተኛው ሙዓዝን ወደ የመን በላኩ ግዜ ይህንን ነገር እንዲህ ሲሉ ገልፀውታል። “አንተ የመፅሀፍ ሰዎች ጋር ትመጣለህ። (አህሉል ኪታብ የሆኑ ሰዎችን ታገኛለህ) ስለዚህም የመጀመሪያው  ጥሪህ ላ ኢላህ ኢለላህ  እና ሙሐመድ የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መመስከር ላይ ይሁን።  ይህ የመጀመሪያው ባሮች ላይ ግዴታ የሚሆነው ጉዳይ  ነው። አላህን በብቸኝነት ማምለክ እና የአላህ መልክተኛ ከአላህ ዘንድ መላካቸውን መመስከር፤ኢኽላስና(አላህን በፍፁምነት መገዛት) ሙታበዓህ(መልክተኛውን መከተል) እነዚህ ነገሮች ማንኛውም አምልኮ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ መስፈርት ሆነው ይቀርባሉ።

ስለዚህም የመጀመሪያው ባሮች ላይ ግዴታ የሆነው ነገር አላህን በብቸኝነት ማምለካቸው፤ መለኮታዊ ተልዕኮ ከጌታቸው እንደተሰጣቸው ለአላህ መልክተኛ መመስከራቸው ነው። ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም ብሎ መመስከር ሁሉንም የተውሒድ ክፍሎችን በውስጡ አቅፎ ይዟል።




Share

ወቅታዊ