Back to Top
ከዚህም በተጨማሪ ጠንቋይ ቤት የሚመላለሱ ሰዎች አስመልክቶ በሸሪዓው ያላቸውን ብያኔ ብናውቅ ጥሩ ይመስለናል?
   ዐቂዳ (እምነት ነክ ጉዳዮች)        ሺርክ (በአምልኮ ማጋራት) እና አይነቶቹ

ጠንቆይ ቤት የሚመላለሱ ሰዎች አስመልክቶ ያለው ብይን


ጥያቄ(33): ከዚህም በተጨማሪ ጠንቋይ ቤት የሚመላለሱ ሰዎች አስመልክቶ በሸሪዓው ያላቸውን ብያኔ ብናውቅ ጥሩ ይመስለናል?
መልስ:

እዚህ ላይ ሰዎች ሦስት አይነት ሁኔታ አላቸው፦

አንደኛው፡ ጠንቋይ ዘንድ በመሄድ በሚለው ነገር ሳይምንበት ወይም ለመፈተንና እርሱን ለሰዎች ማጋለጥ ሳይፈልግበት ቢጠይቀው። ይህ ድርጊት ወንጀል ሲሆን የአርባ ቀን ሰላቱ ተቀባይነት አያገኝም።

ሁለተኛው ደግሞ ፡ ጠይቆት ካመነበት ሲሆን ይህ ተግባር ኩፍር ነው።

ምክንያቱም ቀጣዩን የአላህን ቃል በማስተባበሉ የተነሳ ፦

«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም፡፡ ግን አላህ (ያውቀዋል)፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም» በላቸው፡፡” [አነምል:65]

ሦስተኛው፦ እርሱ (ጠንቋይ) ዘንድ መጥቶ የሚጠይቅበት ዓላማው አጭበርባሪና ቀጣፊ መሆኑን ለሰዎች ለማጋለጥ ከሆነ ይህ ምንም ችግር የለውም ብለናል። እንደሚታወቀው ማንኛውም ነገር ወደ ክልክል ያዳረሰ ከሆነ ያ ነገር ክልክል ይሆናል።

እንበልና በሦስተኛው ሁኔታ ላይ የተጠቀሰው ማለትም የሚጠይቀበት ዓላማ ይህን ጠንቋይ ቀጣፊ መሆኑን ለሰዎች ለማጋለጥ ቢሆ ን ነገር ግን እርሱ ጋ ሲሄድ የተመለከቱት ለዚህ ዓላማ መሄዱን የማያውቁና በመሄዱ የሚሸወዱ ከሆነ በዚህን ግዜ ዓላማው ጥሩ ቢሆንም እንኳ መሄድ የለበትም። ምክንያቱም ማንኛውም ነገር ወደ ክልክል ያዳረሰ ከሆነ ያ ነገር ክልክል ይሆናል፤ የሚል መርህ አለና።




Share

ወቅታዊ