ጥያቄ(32): ጥንቁልና ማለት ምን ማለት ነው?
መልስ:
ጥንቁልና ማለት መሰረት በሌለው ነገር ላይ ሐቅ ላይ ለመድረስ የሚደርግ ግምትና መላምት ነው። በጃሂሊያ ዘመን አንዳንድ ሰዎች እንደ ስራና መተዳዲሪያቸው በመቁጠር ከሸይጧን ጋር በመገናኘት ሸይጣኖች ደግሞ ሰማይ ድረስ በመውጣት ወሬን ሰርቀው ያቀብሏቸዋል፤ እነሱ ደግሞ አንዷን ቃል በመያዝ ከራሳቸው በመጨማመር ለሰዎች ያወራሉ። ምናልባትም የተናገሩት ነገር ተከስቶ ሰዎች ሲያዩ ይሸወዳሉ። በመካከላቸው ለመፋረድ መመለሻም አድርገው ይይዟቸዋል። እንዲሁም ወደፊት ለሚከሰቱ ነገሮች ለማወቅ እነሱጋ ይሄዳሉ።
ለዚህም ሲባል ጠንቋይ ማለት ባጭሩ ወደ ፊት ስለሚከሰት ነገር የሚያወራ ማለት ነው። ወደ ጠንቋይ ቤት የሚሄድ ሰው ለሦስት ይከፈላሉ፦
የመጀመሪው ክፍል ፦ ወደ ጠንቋይ ቤት በመሄድ ስለአንዳች ነገር ጠይቆ ነገር ግን አያምንበትም (ያለውን አይቀበለውም) ይህ ተግባር ሐራም ይሆናል። ይህን ያደረገ ደግሞ ቅጣቱ የአርባ ቀን ሰላቱ ተቀባይነት አያገኝም። በሙስሊም ዘገባ ፀድቆ እንደመጣው የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል ፦ “ጠንቋይ ጋር መጥቶ የጠየቀ የአርባ ቀን ወይም የአርባ ለሊት ሰላት ተቀባይነት አያገኝም።”
ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ፦ ጠንቁይ ቤት መጥቶ ከጠየቀ በኋላ የተናገረውን አምኖ ይቀበለዋል። ይህ በአላህ መካድ (ኩፍር) ነው። ምክንያቱም የሩቅ ምስጥርን አውቃለሁ ብሎ የሚሞግትን እውነት ነው ብሎ መቀበል ቀጣዩን የአላህን አንቀፅ እንደማስተባበል ይቆጠራል።
ለዚህም ሲባል በሰሒህ ሐዲስ ከመለክተኛው እንዲህ የሚል መልክት መጥቷል፦ “ጠንቋይ ጋር በመምጣት ያለውን አምኖ የተቀበለ በሙሐመድ የወረደውን (ቁርኣን) አስተባብሏል።”
ሦስተኛው ክፍል ደግሞ ፦ ወደ ጠንቋይ በመምጣት ሰዎች (የጠንቋይ) ማንነቱን እንዲረዱ እና ጠንቋይ መሆኑን፤ሰዎች ላይ በማመሳሰል እንደሚያሳስትና እንደሚያጠም ለሰዎች ያጋልጥ ዘንድ አንዳንድ ጥያቄዎች ቢያቀርብ ችግር የለውም። ለዚህም ማስረጃው ነቢዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ኢብኑ ሰያድ ዘንድ በመምጣት ወይም ነቢዩ (ሰለለሁ አለይሂ ወሰለም) ኢብኑ ሰያድ ጋር ሄደው በውስጤ ምን ደብቄለሁ? ብለው ጠየቁት። እሱም፦ “ጭስ” አለ ነቢዩም (ሰለለሁ አለይሂ ወሰለም)፦ ዝም በል! ወሰንህን ልታልፍ አትችልም።”
እነዚህ ማለትም ጠንቁይ ጋር መሄድ አስመልክቶ ከላይ ያሳለፍናቸው ሦስት ሁኔታዎች ባጭሩ፦
እርሱ ዘንድ ሄዶ ሳያምንበት መጠየቅ ማለትም በጥያቄው ጠንቋዩን ለመፈተንና እርሱን ለሰዎች ማጋለጥ ሳይፈልግበት። ይህ ሐራም ነው። ቅጣቱም የአርባ ቀን ሰላቱ ተቀባይነት አያገኝም። ሁለተኛው፦ ጠይቆት ካመነበት ይህ ኩፍር ነው። ይህ ሰው ተውበት ማድረግ ይኖርበታል። ያለዚያ በኩፍር ላይ ሞተ ማለት ነው።
ሦስተኛው ሁኔታ ደግሞ ፦ የሚጠይቀው ሊፈትነውና እርሱን(ጠንቋዩን) ለሰዎች ሊያጋልጥ ከሆነ ይህ ችግር አይኖረውም።