Back to Top
እምነት ይጨምራል፤ይቀንሳል የሚለውን አስመልክቶ አንዳንድ ጭፍሮች ኢማን አይጨምርም፤ አይቀንስም የሚል እንዲያውም አንድ ሰው ወንጀል ሲሰራ እምነቱን ሙሉ ለሙሉ ያጣል ብለው ለሚያምኑ ሰዎች ምን አይነት ምላሽ ይሰጣቸዋል?

ጥያቄ(28): እምነት ይጨምራል፤ይቀንሳል የሚለውን አስመልክቶ አንዳንድ ጭፍሮች ኢማን አይጨምርም፤ አይቀንስም የሚል እንዲያውም አንድ ሰው ወንጀል ሲሰራ እምነቱን ሙሉ ለሙሉ ያጣል ብለው ለሚያምኑ ሰዎች ምን አይነት ምላሽ ይሰጣቸዋል?
መልስ:

እነዚህ ሰዎች ላይ ምላሽ የምንሰጠው ከላይ ባሳለፍናቸው የቁርኣንና የሐዲስ መረጃዎች እና ተጨባጫዊ በሆኑ ማስረጃዎች ይሆናል። በተጨማሪም እነዚህን ሰዎች እንዲህ ስንል ጥያቄ እናቀርብላቸዋለን። አንድ ሰው መጥቶ እገሌ የሚባል ሰው እዚህ አገር ዛሬ ገብቷል፤ብሎ እናንተ ዘንድ ታማኝ የሆነ ሰው ቢነግራቹ ያ የተባለው ሰው መምጣት ላይ እምነት ይኖራችኋልን?  ሌላ ሰው በተጨማሪ መጥቶ ያንኑ ቢደግምላቹስ? እምነታቹና እርግጠኝነታቹ አይጨምርምን? በርግጠኝነት መልሳቸው የሚሆነው አዎን ይጨምራል፤ የሚል ይሆናል። ያንን ሰው ሲመጣ በአይናቹ ብትመለከቱትስ? እርግጠኝነታቹ ይበልጥ ይጨምራል እንላቸዋለን። በዚህ ነገር ላይ ማንም አይጨቃጨቅም። በተጨማሪም እንዲህ እንላቸዋለን፦ የኢማን ስያሜ ውስጥ የአንደበት ስራ እና የአካል ተግባርን እስካካካተትን ድረስ አንደበታዊና አካላዊ ስራን አስመልክቶ መጨመርና መቀነስን ማንም የሚያየውና የማያስተባብለው ጉዳይ ነው። ስለዚህም በነዚህ የጥያቄ ምላሾች መሰረት እምነት እንደሚጨምርና እንደሚቀንስ ግልፅ ማስረጃ አለን ማለት ነው።




Share

ወቅታዊ