Back to Top
ዛሬ ላይ እጅግ በርካታ የሆኑ እምነት የሌላቸው ነገር ግን አዲስ ግኝት የሚፈጥሩና አዳዲስ ምርቶችን የሚያመርቱ አዕምሯቸው የላቅ ሰዎች አሉ።ሁላቸውም አላህ የለም በሚለው ላይ ይስማማሉ። እነዚህና መሰሎቻቸው ምን አይነት ምላሽ ነው የሚሰጣቸው?
   ዐቂዳ (እምነት ነክ ጉዳዮች)        የኢማን ምንነት        በአላህ ማመን

እምነተ የሌላቸው ሰዎች (ደህሪዮች) ምን አይነት ምላሽ የሚሰጣቸው?


ጥያቄ(20): ዛሬ ላይ እጅግ በርካታ የሆኑ እምነት የሌላቸው ነገር ግን አዲስ ግኝት የሚፈጥሩና አዳዲስ ምርቶችን የሚያመርቱ አዕምሯቸው የላቅ ሰዎች አሉ።ሁላቸውም አላህ የለም በሚለው ላይ ይስማማሉ። እነዚህና መሰሎቻቸው ምን አይነት ምላሽ ነው የሚሰጣቸው?
መልስ:

በመጀመሪያ እነዚህ አዕምሯቸው የላቀ ነው ባልከው ንግግር ላይ ሀሳብ መስጠት እወዳለሁ። አዕምሮ ስትል ምናልባት መገንዘብና ነገሮችን የመለየት አቅም ከሆነ አዎን ትክክል ነህ። ንገር ግን ለመልካሙ የተመራ ዐቅል ከሆነ ግን እነዚህ ዐቅል አላቸው አይባሉም። ለዚህም ሲባል ከሃዲያን አላህ በቁርኣኑ (እነርሱ) ደንቆሮዎች፣ ዲዳዎች፣ ዕውሮች ናቸው፤ ስለዚህ እነርሱ አያውቁም ዐቅል የላቸውም፡፡ በማለት ይገልፃቸዋል። ይህ ከመሆኑ ጋር ማስረጃን ስምቶ የመረዳት አቅም አላቸው። በእውነቱ ጌታ የለም ብሎ ሽምጥጥ አድርገው የሚክዱት ከኩራት የተነሳ ነው እንጂ ሌላ ምክንያት አይሰጠውም።ምክንያቱ አንድ የቆመ በር እንኳ እራሱን ፈጥሮ ሊቆም እንደማይችል እነሱም የሚያውቁት እውነታ ነው። ከዚህ በር መገኘት ጀርባ አናጢ ወይም በያጅ እንዳለ እና ያንን በር የገጠመ ግንበኛ እንዳለ እነሱም የሚያውቁት እና የሚገነዘቡት እውነታ ነው። እንዲያውም የሚመገቡት እህል የሚጠጡት ውሃ እንኳ ሳይቀር ከሰብልን አውጥቶ ፈጭቶ ወደ ምግብነት የሚቀይረው አካል አለው። በተጨማሪም ይህ አዝርዕት እና ሰብል ግንድና ፍሬዎች ሊኖሩት የቻለው ከመሬት ተነስቶ እንዳልሆነ ማንም ሰው የሚረዳውና የሚገነዘበው እውነታ ነው። ይህ አይነቱ አበቃቀል የሰው ልጅ ሊያበቅለውና ሊሰራው እንደማይችል የሰው ልጅ ያውቀዋል።ነገር ግን ከኩራት የተነሳ ይህን ሁሉ እውነታ አይቀበሉም። ኩራተኛ ወይም እብሪተኛ ሰው ደግሞ ከሱጋር በመረጃ ማውራት ምንም አይፈይድም። ከፊት ለፊቱ ያለችውን ጸሐይ እንኳ ይህች ጸሀይ ናት ብለህ ብታስረዳው እንኳ አይደለችም ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ ይክድሃል። ከነዚህ ሰዎች ጋር መከራከር ጊዜን በከንቱ ከማሳለፍ ነው የሚቆጠረው። አንዳንድ ኡለማዎች እንዳሉት ለእነሱ ጥሪ የሚደረግላቸው መወያየት ሳይሆን ዱላን መጠቀም ነው የሚበጀው።
Share

ወቅታዊ