Back to Top
ዒባዳ ዒባዳ ለመሆኑ ልናውቅበት የምንችለበት የራሱ ፅንሰ ሀሳብ ይኖረው ይሆን? ጥቅል አሊያም ለየት ያለ ግንዛቤ አለውን?

ጥያቄ(2): ዒባዳ ዒባዳ ለመሆኑ ልናውቅበት የምንችለበት የራሱ ፅንሰ ሀሳብ ይኖረው ይሆን? ጥቅል አሊያም ለየት ያለ ግንዛቤ አለውን?
መልስ:

አዎን። ጥቅላዊ የዒባዳ ፅንሰ ሀሳብ ከላይ ቀደም ሲል ጠቁሜዋለሁ። እርሱም (ዒባዳ) አምልኮት ማለትም ሸሪዓው ላይ በመጣው መሰረት አላህን በመውደድና ትዕዛዙን በማላቅ ክልከላውን በመራቅ ለአላህ እራስን ዝቅ ማድረግ ወይም ማስተናነስ ዒባዳ ይባላል። ይህ ጥቅላዊ የዒባዳ መልዕክት ሲሆን ለየት ያለው ፅንሰ ሐሳቡ ደግሞ ማለትም ዒባዳ ሲብራራ ፦ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዳሉት ፦ “አምልኮ ማለት ማንኛውም አላህ የሚወደውንና የሚደሰትበት ውጫዊና ውስጣዊ ንግግርና ተግባር የሚያጠቃልል ስያሜ ነው። ለምሳሌ ስጋት፤እውቀትን ያማከለ ፍራቻ፤መመካት፤ሰላት፤ ዘካት፤ጾም እና ሌሎች የኢስላም ሸሪዓዊ ድንጋጌዎች …  ወዘተ ይገኙበታል።

የዒባዳ ፅንሰ ሐሳቡ ጥቅልና ለየት ባለ መልኩ ስትል ምናልባት ከፊል ዓሊሞች ዒባዳን ዒባዳ ከውኒያህ እና ዒባዳህ አሸርዒያህ ብለው የሚከፍሉት ነገርን ለመጠየቅ ፈልገህ ከሆነ ይህ ማለት የሰው ልጅ ከውኒይ (ይሁንታዊ)፤ ሳይወድ በግድ ለጌታው ማጎብደድ ወይም ሸሪዓዊ፤ በፍላጎትና በራሱ መነሳሳት የሚሰራው የአምልኮ ዘርፍ አለ። ከውኒይ (ይሁንታዊ) ዒባዳ ሁሉንም ፍጥረታት ያጠቃለለ ነው። አማኝን እና ከሃዲ፤ በጎ አድራጊውንና ጠማማውን የሚያካተት የአምልኮ ዘርፍ ነው።
ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏልና ፦

“በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ (በትንሣኤ ቀን) ለአልራሕማን ባሪያ ኾነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡” [መርየም:93]

ማንኛውም በሰማያትም ሆነ በምድር የሚኖር ነገር በሙሉ ሳይወድ በግድ ከውኒይ በሆነ መልኩ እራሱን ያስጎበድዳል። አላህን መፃረር በፍፁም አይችልምና። ወይም አላህ በይሁንታዊ ፍላጎቱ (ኢራደቱ አልከውኒያህ) መቃወም ማንም አይቻለውም።

“ዒባዳ ኻሳህ” ለየት ባለ መልኩ የሚፈፀም የአምልኮ አይነት ደግሞ ፡ “ዒባደቱ አሸርዒያህ” ይባላል። እርሱም በፍቃደኝነትና በውዴታ እራስን ለአላህ ማስገዛት ሲሆን በአላህ ያመኑ እና ትዕዛዙን በአግባቡ የተወጡ ምእመናን ብቻ ላይ የተገደበ ነው። ከእንደገናም የ ”ኻስ” ኻስ አለው ከ”ኻስም” በላይ አለ።  እጅግ ፍፁም የሆነ አምልኮ ኻሱል አኸስ የሚባለው የዒባዳ ዘርፍ መልክተኞች የሚፈፅሙት የዒባዳ አይነት ነው።
ለምሳሌ አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፦

“ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ያወረደው (አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው፡፡” [ አልፉርቃን :1]

 

እንዲህም ይላል፦ “በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾኑ … “ [አል በቀራ :23]

 

እንዲህም ይላል፦ ”ባሮቻችንንም ኢብራሂምን፣ ኢስሐቅንና ያዕቆበንም … አውሳላቸው፡፡” [ሷድ :45]

ሩሱሎች (መልክተኞች) ፍፁማዊ ባርነት ለአላህ እንዳላቸው የሚጠቅሱ ሌሎችም አንቀፆች አሉ። 


 
Share

ወቅታዊ