ጥያቄ(17): ይህ የኢማን ፅንሰ ሀሳብ ጂብሪል ሐዲስ ላይ ጂብሪል ስለ ኢማን ሲጠይቃቸው ከሰጡት መልስ ጋር ተያያዥነት አለውን?
መልስ:
አዎን። አንድ ሰው በአላህ መኖር ጌትነት አምላክነት፤ በመላክት መኖር፤ በመጽሃፍት መወረድ እና በመልክተኞች መላክ ሲያምን እነዚህ የሚጠቁሟቸውን መልክቶች መቀበልና መፈፀም ይኖርበታል። ይህን ካላደረገ በምላሱ ብቻ መናገሩ አይፈይደውም። እንዲሁም ልቡ ውስጥ ያለው እምነትም ካልታዘዘና ካልተገበረ አይጠቅመውም።