Back to Top
የኢማን ፅንሰ ሀሳብና ማዕዘኖቹ ምን እንደሆኑ በአጭሩ ቢያብራሩልን።

ጥያቄ(16): የኢማን ፅንሰ ሀሳብና ማዕዘኖቹ ምን እንደሆኑ በአጭሩ ቢያብራሩልን።
መልስ:

ኢማን ሁለት ፅንሰ ሀሳቦች አሉት።  አንደኛው ቋንቋዊ ፅንሰ ሀሳብ ሲሆን አንድን ነገር ማመንና ማረጋገጥ የሚል መልክት አለው። ሌላኛው ደግሞ ሸሪዓዊ ፅንሰ ሀሳብ ነው። እምነቱ የሚያዛቸውን መቀበልና መተግበር ውስጡ ያካተተ ማረጋገጥ ኢማን ይባላል። አንድ ሰው በአንደበቱ የሚመሰክራቸውን ነገሮችን ካልተቀበለና ወደ ተግባር ካለወጠ በምላሱ መናገሩ ብቻ በቂ አይደለም።

ለምሳሌ፦ ሙሀመድ የአላህ መልክተኛ ናቸው ብሎ ከመሰከረ በኋላ መልክተኛው ይዘውት የመጡትን መልክት የማይቀበልና ለትዕዛዛቸው እጅ የማይሰጥ ከሆነ አማኝ አይባልም። ለዚህም ሲባል ከሙሽሪኮች መካከል መልክተኛው ትክክለኛ መልክተኛ መሆናቸውን የመሰከሩና ያረጋገጡ ነበሩ። ነግር ግን የወገኖቻቸውን እምነት ላለመልቀቅ በዛው እምነት ላይ ቀጠሉ መልክተኛውን አልታዘዙም። ስለዚህም ለመልክተኛው እጅ ሳይሰጡና ትዕዛዛቸውን ሳይተገብሩ በምላስ ወይም በቀልብ ብቻ ማረጋጣቸው አልጠቀማቸውም። ኢማን በሸሪዓ ያለው ፅንሰ ሀሳብ ከቋንቋዊ ኢማን ፈፅሞ የተለየ ነው። ምናልባትም በሸሪዓ የኢማን ፅንሰ ሀሳብ ከቋንቋዊ የኢማን ትርጓሚ ሰፋ ያለና ብዙ ነገሮችን በውስጡ ያካተተ ነው። ለምሳሌ ሰላት ከሸሪዓዊ ኢማን ውስጥ የሚካተት ነው። አላህ እንዳለው፦

“ አላህም እምነታችሁን (ስግደታችሁን) በከንቱ የሚያስቀር አይደለም።” [አልበቀራ:143]

ይህም ማለት  ቁድስ የሙስሊሞች ቂብላ በነበረችበት ወቅት ወደርሷ ዞራችሁ የሰገዳችሁት ሰላት ምንዳችሁን አያስቀርባችሁም ማለት ነው። ነገር ግን ሰላት ውጫዊ ተግባር በመሆኑ በቋንቋ ኢማን አይባልም። ኢማን በቋንቋ ውስጣዊ ተግባሮችን ብቻ የሚመለከተው ነው። ስለዚህም ኢማንን በሸሪዓ መተረጎም ስንፈልግ፦ ኢማን ማለት በውስጡ የሚጠቁማቸውን መልክቶች መቀበልና መፈፀምን ያቀፈ ማመንና ማረጋገጥ ማለት ነው እንላለን። ይህንን መልዕክት በውስጡ ካልያዘ በሸሪዓው ኢማን አይሰኝም።
Share

ወቅታዊ