Back to Top
ትጥበትን ግዴታ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል ጀናባን ጠቅሰዋል፤ ጀናባን አስመልክቶ የሚጠቀሱ ህግጋቶች ምንድን  ናቸው?

ጥያቄ(78): ትጥበትን ግዴታ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል ጀናባን ጠቅሰዋል፤ ጀናባን አስመልክቶ የሚጠቀሱ ህግጋቶች ምንድን  ናቸው?
መልስ:

ከጀናባ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ህግጋት የሚከተሉት ናቸው።

አንደኛ፡ ጁኑብ የሆነ ሰው ሰላት መስገድ በሱ ላይ ሀራም ነው።

ሁለተኛው፡ በከዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ በሱ ላይ ክልክል ነው።

ሦስተኛው፡ ቁርኣን መንካት ክልክል ነው።

አራተኛው፡ ያለውዱእ መስጂድ ውስጥ መቀመጥ ክልክል ነው።

አምስተኛው፡ ገላውን እስካልታጠበ ቁርኣን ማንበብ አይችልም።

ከጀናባ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ህግጋት እነዚህ አምስት ድርጊቶች ናቸው።




Share

ወቅታዊ