ጥያቄ(72): ትጥበትን ግዴታ የሚያደርጉ ነገሮች ምን ምን ነገሮች ናቸው? አስተጣጠቡስ?
መልስ:
አስተጣጠቡን አስመልክቶ ሁለት አይነት ሲሆን ግዴታዊ አስተጣጠብና የተሟላ (ተወዳጅ) አስተጣጠብ ናቸው።
ግዴታዊ አስተጠጠብ፤ ሙሉ ገላን ውሃ በማዳረስ ማጠብ፣ከዚህም ጋር መጉመጥመጥ፣በአፍንጫ ውሃ ማስገባትና ማስወጣት ያካትታል። በየትኛውም ሁኔታ ይሁን መላ አካሉን በውሃ ካዳረሰ ትልቁ ሐደስ (ጀናባ) ይነሳለታል።
ሁለተኛው አስተጣጠብ የተሟላ አስተጣጠብ ሲሆን እርሱም መልዕክተኛው(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንደታጠቡት አስተጣጠብ መታጠብ ነው።
መልክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ከጀናባ ትጥበት ሲታጠቡ፤ መጀመሪያ መዳፋቸውን ያጥባሉ፣ከዚያም ሀፍረታቸውን ፣ቀጥሎም በጀናባው የተነካካውን የሰውነት ክፍል ያጥባሉ። ከዚያም የውዱእ አደራረግ ላይ በጠቀስነው መሰረት ሙሉ ውዱእን ያደርጋሉ። ከዚያም ራሳቸውን ውሃ እንዲደርስ አድርገው ሦስቴ ያጥባሉ፣ቀጥሎም የተቀረውን ገላቸውን ያጥባሉ። የተሟላው አስተጣጠብ ይህን ይመስላል።
ትጥበትን ግዴታ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል፦ በእውን ይሁን በእንቅልፍ ልብ የፍትወት ውሃን ማፍሰስ፣ ነገር ግን በእንቅልፍ ልብ ሲሆን የዘር ፈሳሽ ሲፈሰው ስሜት ባይኖረውም መታጠብ ግዴታ ነው። ምክንያቱም እንቅልፍ ላይ ያለ ሰው ሳይታወቀው የዘር ፈሳሽ ሊፈሰው ይችላልና። በየትኛውም ሁኔታ ላይ ሆኖ በስሜት ፈሳሽ ከወጣው ትጥበት ግዴታ ነው።
ሁለተኛው ትጥበትን ግዴታ የሚያደርገው ነገር ደግሞ፦ ግብረ ስጋ ግንኙነት ነው፤ ባል ህጋዊ ሚስቱን ከተገናኘ ሁለትም ላይ ትጥበት ግዴታ ነው። ግንኙነት የሚከሰተው የወንዱ ብልት ጫፍ ከሴቷ ብልት ከተነካካ ሁለቱም ትጥበት ግዴታ ይሆንባቸዋል። ምክንያቱም የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋልና፦ “በውሃ ትጥበት ግዴታ የሚሆነው ውሃ(የዘር ፈሳሽ ሲገኝ) ነው።” ሌላኛው ሐዲስ ላይ ደግሞ ፦ “ባል ሚስቱ አራት ቅርንጫፍ(የሰውነት ክፍል፤ ሁለት እግሮችን ሁለ እጆች መካከል) ላይ ሆኖ ከዚያም ከታገላት (በሁለቱም) ላይ ትጥበይ ግዴታ ይሆናል፤ ባያፈስም።” ብለዋል።
ይህ ቁም ነገር ማለትም የዘር ፈሳሽ ባያፈሱም መታጠብ እንደሚገባ ከብዙ ሰዎች ሸሪዓዊ ብይኑ የተሰወረ ነው። አንዳንድ ሰዎች ምናልባትም ሚስቱን ለወር ወይም ለሳምንት ያህል ይገናኝና የዘር ፈሳሽ ስላልፈሰሰው ባለማወቅ ትጥበት የማይፈፅም አለ። ይህ ጉዳይ እጅግ አደገኛ ጉዳይ ነው። ስለዚህም በሰዎች ላይ አላህ በመልክተኛው ላይ ያወረደውን ሸሪዓ ጠንቅቆ ማወቅ ግዴታ አለባቸው። ስለሆነም ከላይ ያሳለፍነው የሐዲስ መረጃ መሰረት አንድ ሙስሊም ሚስቱን ከተገናኝ ባያፈስም እንኳ በርሱም ሆነ በሚስቱ ላይ ትጥበት ግዴታ ይሆናል።
ትጥበትን ግዴታ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል፦ የወር አበባ ደምና የወሊድ ደም መፍሰስ ናቸው። አንዲት ሴት የወር አበባ ደም ከፈሰሳት በኋላ ከደሙ ከፀዳች ትጥበት በሷ ላይ ግዴታ ይሆናል። ለሚከተለው የአላህ ቃል ሲባል ፦
በተጨማሪም የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) የበሽታ ደም ያለባት ሴት የወር አበባ ጊዜዋን ቆጥራ ከጨረሰች በኋላ እንድትታጠብ አዘዋታል። የወሊድ ደም ላይ ያለች ሴትም እንዲሁ ደሙ ሲቆምላት መታጠብ ይኖርባታል።
አንዲት ሴት ከወሊድ ደም እና ከሀይድ ደም ስትጠራ የምትታጠበው አስተጣጠብ እንደ ጀናባ ትጥበት ነው። ሆኖም አንዳንድ ዑለማዎች አንዲት ሴት ከሀይድ ስትጠራ ይበልጥ ንፅህና እና ፅዳት ይገኝላት ዘንድ በሲድር(ቁርቁራ) ቅጠል መታጠብ ይወደዳል ይላሉ።
አንዳንድ ዑለማዎች ትጥበትን ግዴታ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል ብለው ከጠቀሷቸው ውስጥ ሟችን ማጠብ ይገኝበታል። ማስረጃቸውም፦ መልክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ልጃቸው በሞተች ጊዜ ሲያጥቧት ለነበሩ ሴቶቹ፦ “ሦስቴ እጠቧት፣ወይም አምስት፣ወይም ሰባት ወይም አስፈላጊ ሆኖ ከታያችሁ ከዚያም በላይ እጠቧት።” እንዲሁም ዐረፋ ላይ ሳለ ከፈረሱ ላይ ወድቆ የሞተውን ሃጅ ላይ የነበረውን ሰው አስመልክቶ ለአጣቢዎቹ የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲህ ብለዋቸዋል፦ “በውሃና በቁርቁራ እጠቡት፤በሁለት ዝርግ ጨርቆች ከፍኑት(ገንዙት)።” ስለዚህም ዑለማዎች ሟች መሞቱ ትጥበት ግዴታ የሚያደርግ ክስተት ነው ይላሉ። ሆኖም ትጥበቱ ግዴታ የሚሆነው በህይወት ያሉ ሰዎች ላይ ነው ሟች በመሞቱ ግዴታው ከርሱ ላይ ተነስቶለታል። ትጥበቱ ግዴታ የሚሆነው በህይወት ያሉ ሰዎች ላይ ነው ሲባል በህይወት ላይ ያሉ ሰዎች ሟችን ማጠብ ትዕዛዙ እነሱን ነው የሚመለከተው፤ ስለዚህም በህይወት ያሉ ሰዎች ሟችን ማጠብ በነሱ ላይ ግዴታ ስለሆነ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። መልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ይህን እንዲያደርጉ አዘዋቸዋልና።