Back to Top
ሁለት ጆሮዎች ሲታበሱ ለብቻ ውሃ ይያዛልን? ወይንስ ለራስ ቅል በተያዘው በዚያው አንድ ላይ  ጆሮዎቹ ይታበሳሉ?

ጥያቄ(69): ሁለት ጆሮዎች ሲታበሱ ለብቻ ውሃ ይያዛልን? ወይንስ ለራስ ቅል በተያዘው በዚያው አንድ ላይ  ጆሮዎቹ ይታበሳሉ?
መልስ:

ጆሮን ለማበስ አዲስ ውሃ መያዝ ግዴታ አይሆንም።እንዲያውም አይወደድም። ምክንያቱም የነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) የውዱእ አደራረግን የዘገቡልን ሰሓቦች መልክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ጆሯቸውን ለማበስ አዲስ ውሃ እንደሚይዙ አልዘገቡልንም፤ስለዚህም ራስቅሉን ሲያብስ በረጠበው እጁ በዚያውም ጆሮዎችን ማበሱ በላጭ ተግባር ነው።




Share

ወቅታዊ