Back to Top
ድግምት እና ድግምትን መማር በሸሪዓው ያለው ብይን ምንድ ነው?
       ሺርክ (በአምልኮ ማጋራት) እና አይነቶቹ

ድግምት እና ድግምትን መማር በሸሪዓው ያለው ብይን


ጥያቄ(40): ድግምት እና ድግምትን መማር በሸሪዓው ያለው ብይን ምንድ ነው?
መልስ:

ሲሕርን(ድግምት) መማር ሐራም ነው። እንዲያውም ከሸይጣን ጋር መተጋገዝ ከታከለበት ኩፍር ይሆናል። አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦

“ሰይጣናትም በሱለይማን (ሰሎሞን) ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን (ድግምት) ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ (ድግምተኛ አልነበረም)፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩትና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር (ያስተምሩዋቸዋል)፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ፡፡ እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም፡፡ የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውንም ይማራሉ፡፡ የገዛውም ሰው ለርሱ በመጨረሻይቱ አገር ምንም እድል የሌለው መኾኑን በእርግጥ ዐወቁ፡፡” [አልበቀራ:102]

 ይህ አይነቱ የድግምት አይነት ማለትም ከሸይጣን ጋር በመተባበር ድግምት መስራትን መማር ኩፍር ነው። የተማሩትንም ድግምት ተግባር ላይ ማዋልም ኩፍር ነው፤ ሰዎች ላይ በደልና ግፍ እንደማድረስ ይቆጠራል። ስለዚህም ድግምተኛ በሸሪዓው ካፊር ነው በሚል ወይም ቅጣቱን ያገኝ ዘንድ ይገደላል። ድግምቱ ኩፍር ደረጃ የሚያደርሰው ከሆነ ካፊር ነው በሚል ብይን ይገደላል።ድግምቱ ኩፍር ደረጃ የማይደርስ ከሆነ ቅጣቱን ያገኝ ዘንድ እና ሙስሊሞችን ከርሱ ጉዳትና ከሚያደርስባቸው ችግር ለመገላገል ሲባል ይገደላል።




Share

ወቅታዊ