ጥያቄ(35): ይህ አይነቱ ትንበያ ፍጥረተ ዓለሙ ላይ የሚከሰቱ የአላህ ሱናዎች (ልማዳዊ አሰራር) በማስተዋልና ክትትል በማድረግ የሚመጣ ነው ማለት ነው ብለን መናገር እንችላለን? መልስ:
አዎን። ይህ ማለት ፀሐይ ወደ መጥለቂያዋ ስታዘነብል የዙሑር ወቅት ደርሷል ብለን እንደምንናገረው ማለት ነው። ፀሐይ ስትጠልቅ ደግሞ መግሪብ ሰላት ገብቷል ወዘተ …. ብለን እንደምንተነብየው ማለት ነው።