Back to Top
በዳይንና አመፀኛ አስመልክቶ ተቀራራቢ ወይም አንዱ ሌላውን የሚተካ ነገር እንደሆነ ጠቅሰውልናል፤ እርሱም በዳይ የሚለውን ሲገልፁ አላህ ካወረደው ውጭ የሚፈርደው የአላህ ህግ የበላይ መሆኑን ያውቃል ነገር ግን አንድን ሰው መበቀል ስለሚፈልግ የአላህን ህግ ትቶ በሌላ ይፈርዳል። ፋሲቅ(አመፀኛ) ደግሞ የአላህን ህግ ያውቃል፤የአላህ ህግ ትክክል መሆኑንም ይረዳል። ነገር ግን ለራሱ ስሜት ወይም ለርሱ ጥቅም ወይም የሌላ ሰው ዝንባሌን ለመግጠም ሲል አላህ ካወረደው ውጭ ይፈርዳል። ስለዚህም በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድ ነው?
   ዐቂዳ (እምነት ነክ ጉዳዮች)        የኢማን ምንነት

በዳይና አመፀኛ መካከል ያለው ልዩነት


ጥያቄ(31): በዳይንና አመፀኛ አስመልክቶ ተቀራራቢ ወይም አንዱ ሌላውን የሚተካ ነገር እንደሆነ ጠቅሰውልናል፤ እርሱም በዳይ የሚለውን ሲገልፁ አላህ ካወረደው ውጭ የሚፈርደው የአላህ ህግ የበላይ መሆኑን ያውቃል ነገር ግን አንድን ሰው መበቀል ስለሚፈልግ የአላህን ህግ ትቶ በሌላ ይፈርዳል። ፋሲቅ(አመፀኛ) ደግሞ የአላህን ህግ ያውቃል፤የአላህ ህግ ትክክል መሆኑንም ይረዳል። ነገር ግን ለራሱ ስሜት ወይም ለርሱ ጥቅም ወይም የሌላ ሰው ዝንባሌን ለመግጠም ሲል አላህ ካወረደው ውጭ ይፈርዳል። ስለዚህም በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድ ነው?
መልስ:

በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ዟሊም (በደለኛ) ብለን የገለፅነው የሚፈረድበት ሰው ላይ በደልን በመሻቱ ምንም የሚያገኘው ጥቅም ስላለው ሳይሆን ለሚፈረድለትም ሰው የሚያገኘውን ጥቅም በማየትም ሳይሆን ዋናው የሚያሳስበው በደልንና ግፍን ተበዳይ ላይ ማድረስ ብቻ ነው የሚፈልገው። በደል ያልነው ከሚፈርድበት(ከተበዳይ) አንፃር ነው። ሌላኛው ግን ለሚፈረድለት አካል መጥቀም እንጂ የሚፈረድበት አካልን በፍርዱ እንደሚጎዳ ወይም እንደሚበደል አያስበውም። ስለዚህም ተበዳይ ማንም ይሁን ማን አያሳስበውም (እርሱ ጋ ለውጥ የለውም) እርሱ የሚሻው የሚፈረድለት አካል ወይም እርሱ መጠቀሙ እንጂ ሌላው አካል መጉዳት ፈልጎ አይደለም። ይህ ነው በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት።
Share

ወቅታዊ