Back to Top
የሰላት አሰጋገድ እና የሰላት ማዕዘናትን አውቀናል። ሰላት ውስጥ ዋጂብ የሆኑ ተግባሮች ምን ምን እንደሆኑ ማወቅ እንፈልጋለን።

ጥያቄ(100): የሰላት አሰጋገድ እና የሰላት ማዕዘናትን አውቀናል። ሰላት ውስጥ ዋጂብ የሆኑ ተግባሮች ምን ምን እንደሆኑ ማወቅ እንፈልጋለን።
መልስ:

የሰላት ዋጂባት የሚባሉት፤ ሰላት ውስጥ ያሉ ተግባሮች እና ንግግሮች ሲሆኑ አንድ ሰው እያወቀ ከተዋቸው ሰላቱ ይበላሽበታል። ረስቶ ከተዋቸው ግን በሱጁድ ሰህው ይጠገናሉ (ይካካሳሉ)። ዋጂብ ከሆኑ ተግባሮች መካከል፤ከተክቢረተል ኢህራም ውጭ ያሉ ተክቢራዎች በሙሉ የሰላት ዋጂብ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው። ተክቢረተል ኢህራም ግን የሰላት ሩክን (ማዕዘን) ሲሆን ሰላት ያለእሱ ሊጀመር ወይም ሊፈፀም አይችልም። ከነዚህ ተክቢራዎች መካከል ሩኩዕ ለማድረግ የሚደረገው ተክቢራ ተለይቶ ይወጣል። ይህም ማለት አንድ ሰጋጅ ኢማሙ ሩኩዕ እያደረገ ሳለ ቢደርስ ተስተካክሎ ከቆመ በኋላ ተክቢረተል ኢህራም አድርጎ ወደ ሩኩዕ ቢወርድ ይህን ሰው አስመልክቶ ፉቀሃዎች፤ለሩኩዕ የሚደረገው ተክቢራ ለዚህ ሰው ብቻ ሱና ነው በሚል አረጋጠዋል።

ከሰላት ዋጂባት መካከል፤ሱጁድ ላይ እና ሩኩዕ ላይ የሚደረጉ ዚክሮች (ተስቢሆች) ሩኩዕ ላይ፤ “ሱብሃነ አላሂ አል ዐዚም” ሲሆን ሱጁድ ላይ ደግሞ "ሱብሃነ ረቢየል አዕላ" የሚለው ዚክር።

ከሰላት ዋጂባት መካከል፤የመጀመሪያው ተሸሁድ እና ለእሱ መቀመጥ።

ከሰላት ዋጂባት መካከል፤በተጨማሪም ተስቢህና ተሕሚድ ይገኙበታል። ማለትም ከሩኩዕ ብድግ ሲባል “ሰሚዐላሁ ሊመን ሀሚዳህ” እንዲሁም ለአሰጋጁም ሆነ ለብቻው ለሚሰግድ ሰው “ረበና ወለከል ሐምድ” የሚለው ዚክር። ኢማምን ተከትሎ  የሚሰግድ ሰው “ረበና ወለከል ሐምድ” ማለት አለበት።(ሰሚዐላሁ ሊመን ሀሚዳህ አይልም)

እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው የሰላት ዋጂባት ሲሆኑ አንድ ሰው እያወቅ ከተዋቸው ሰላቱ ይበላሻል፤ሆኖም ረስቶ ከተዋቸው ሰላቱ ትክክል ነው አይበላሽም። በሱጁድ ሰህው ይጠገናል። ማስረጃውም ዐብዱላሂ ኢብኑ ቡሀይና ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦ መልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዙህር እየሰገዱ ሳለ  ሁለተኛው ረከዓ ላይ መቀመጥን ረስተው ወደ ሦስተኛው ረከዓ ብድግ አሉ። ሰግደው ካበቁ በኋላ ሰዎች እስኪያሰላምቱ ጠብቀው ሁለት ሱጁድ ማለትም ሱጁድ ሰህው ወርደው አሰላመቱ።




Share

ወቅታዊ