Back to Top
ከነቢዩ ሙሐመድ  በኋላ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለስንት አንጃ ተከፋፈለ?
   ዐቂዳ (እምነት ነክ ጉዳዮች)

ሙስሊሙ ለብዙ አንጃ እንደሚከፋፈል


ጥያቄ(52): ከነቢዩ ሙሐመድ  በኋላ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለስንት አንጃ ተከፋፈለ?
መልስ:

ነቢዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በትክክለኛ ዘገባ ፀድቆ በመጣው ሐዲስ መሰረት ፦

"አይሁዳዎች ለሰባ አንድ አንጃ ተከፋፈሉ፤ ክርስቲያኖች ደግሞ ለሰባ ሁለት አንጀዎች ተከፋፈሉ፤ ይህ ሙስሊሙ ህዝብ ደግሞ ለሰባ ሦስት ቦታ ይከፋፈላል፡፡ አንዷ አንጃ ስትቀር ሁሉም የእሳት ናቸው። ሰሓቦችም፦ “ከእሳት ነፃ የምትወጣዋ አንጃ ማን ናት?” ብለው ጠየቁ። እሳቸውም፦ “እኔና ባልደረቦቼ ባለንበት መንገድ ላይ ያሉ ሲቀሩ” በማለት መለሱላቸው፡፡” ይህችም ቡድን “ፊርቀት ናጂያ” ናት። ዱንያ ላይ ከቢድዓ ነፃ የወጣች ስትሆን በአኼራ ደግሞ ከጀሀነም እሳት ነፃ ትወጣለች። እርሷም እስከ እለተ ቂያማ የአላህ እርዳታ የማይለያት ጭፍራ ናት። የአላህን ትዕዛዝ በመፈፀም የበላይ ከመሆን አይወገዱም።"

ከነዚህ ሰባ ሦስት አንጃዎች አንዷ ብቻ ናት ሐቅ ላይ ያለችው።ሌሎቹ ባጢል ላይ ናቸው። አንዳንድ ሰዎች እነዚህን አንጃዎች ለመቁጠር ሙከራ አድርገዋል። ዋነኛ የቢድዓ ቅርንጫፎች አምስት ናቸው ካሉ በኋላ ከያንዳንዱ ቅርንጫፍ ስር ሌሎች ቅርንጫፎችን በመቁጠር ነቢዩ ያሉት ቁጥር (72) ላይ ለማድረስ ሙከራ የሚያደርጉ አሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ አንጃዎችን ከመቁጠር መታቀቡ ይበጃል ይላሉ። ምክንያቱም ባጢል ላይ ያሉት እነዚህ አንጃዎች ብቻ ሳይሆን ከነዚህ በኋላ የመጡ አንጃዎች ከመጀመሪያዎች በባሰ መልኩ ጥመት ላይ የወደቁ አንጃዎች አሉ። አንጃዎቹ በሰባ ሁለት አንጃ ላይ ተቆጥረው ከተገደቡ በኋላ ሌሎች ጠማማ ጭፍራዎች ተፈጥረዋል። ይህ የተገደበው ቁጥር ላይ መድረሱ የሚታወቀውና መጨረሻ ሊኖረው የሚችለው ቂያማ ሊቆም መቃረቢያ እና በመጨረሻው ወቅት ላይ ብቻ ነው።

ስለዚህም መልክተኛው (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በጥቅል ያስቀመጡትን ነገር በጥቅሉ መቀበል በላጭ ነው። ሙስሊሙ ህዝብ ለሰባ ሦስት ጭፍራ ይከፈላል እንላለን። አንዷ ስትቀር ሁሉም የእሳት ናቸው። በተጨማሪም ማንኛውም ነቢዩን (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እና ሰሓቦች የነበሩበትን መንገድ የጣሰ በሙሉ ከነዚህ ጠማማ የእሳት አንጃዎች ይመደባል እንላለለን። ምናልባትም መልዕክተኛው ከጠቀሷቸው መሰረታዊ መርሆች በመነሳት አስር የሚደርሱ አንጃዎች ብቻ ልናውቅ እንችል ይሆናል። ምናልባትም በከፊል ሊቃውንት አቋም መሰረት አንዳንድ አጠቃላይ ከሆኑ ነቢያዊ መርሆች ስር ሌሎች ቅርንጫፎች ሊካተቱ ይችሉ ይሆናል። ትክክለኛው እውቀት አላህ ዘንድ ነው!
Share

ወቅታዊ