Back to Top
 በኹፍ ላይ ማበስ ሸሪዓዊ ሁክሙ እና  መስፈርቶቹ ምን ምንድን ናቸው?

ጥያቄ(73):  በኹፍ ላይ ማበስ ሸሪዓዊ ሁክሙ እና  መስፈርቶቹ ምን ምንድን ናቸው?
መልስ:

በኹፍ ላይ ማበስ በብዙ ሰነድ የተዘገቡ ሐዲሶች ማስረጃ ሆነው ከመጡባቸው  ነገሮች መካከል አንዱ ነው።

በብዙ ሰነዶች ተዘግበው ከመጡ ነገሮች መካከል “በኔ ላይ እያወቅ የዋሸ መቀመጫውን እሳት ያድርግ።” የሚለው ሐዲስና “መስጂድ የገነባ ….”፤በአኼራ አላህ እንደሚታይ የሚዘግበው ሐዲስ፣ ምልጃ እና ሐውድ እንዳለ የሚዘግበው ሐዲስ እና በኹፍ ላይ ማበስ … በብዙ ሰነደች ከተዘገቡ ከፊል መረጃዎች መካከል እነዚህ  ሐዲሶች ይገኙበታል።

እንዲያውም በኹፍ ማበስ እንደሚቻል የቁርኣን ማስረጃ  አለው  አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ)  እንዲህ ይላል፦ “ፊቶቻችሁን፣ እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡ ራሶቻችሁንም (በውሃ) አብሱ፡፡ እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)፡፡” [አልማኢዳ፡6]

(وَأَرْجُلِكُمْ)በከስራ ሲነበብ  ትክክለኛውና ከሰባቱ የአነባበብ ስልት አንዱ ነው። ራሳቹን አብሱ የሚለው ቀጥሎ እግሮቻችሁን የሚለው እግርም እንደ ሆኔታው እንደሚታበስ ይጠቁማል። በዚህም የአነባበብ ስልት ራሳቹን እና እግራቹን አብሱ የሚል ትርጉም ይሰጠናል። እንደሚታወቀው ማበስና ማጠብ ተቃራኒ ተግባሮች ናቸው። ስለዚህም በፈትሃ ሲነበብ  እግር መታጠብ እንዳለበት የሚጠቁመው አንቀፅ እንዲሁ አንድ ሁኔታ ላይ ደግሞ  መታበስን ይጠቁማል። ሁለቱም አፈፃፀሞች ሁኔታዎች ያሏቸው ሲሆኑ መች እና እንዴ የሚለው በሐዲስ ተብራርቶ ይገኛል። ስለዚህም እግሮች ከካልሲና ከኹፍ ገላጣ ሲሆን የሚታጠቡ መሆናቸው፤ እግሮች በካልሲና በኹፍ ሲሸፈኑ መታበስ እንዳለባቸው ሐዲሶቹ ይጠቁማሉ። ይህ የማስረጃ አጠቃቀም ላስተዋለው ግልፅ ነው።

ያም ሆነ ይህ መታበስ ያለበት እግሮች ካልሲ እና ኹፍ ሲያጠልቁ ነው። ኹፍ ላይ ማበስ እንደሚቻል ምንም ጥርጥር የለውም፤ ለዚህም ኢማሙ አሕመድ " በኹፍ ላይ ማበስ ላይ ቅንጣት ታክል ጥርጥር ልቤ ላይ የለም" ያሉት። ነገር ግን በኹፍ ላይ ማበስ ይበቃ ዘንድ መስፈርቶች መኖር ግዴታ ነው።

የመጀመሪያው መስፈርት፦ ( ከጀናባ እና ውዱን ከሚያስደርጉ ነገሮች) ሙሉ ጠሃራ መሆን አለበት። ማስረጃውም፦ ሙጊራ ኢብ ሹዕባ ያስተላለፉት ሐዲስ ነው። እንዲህ ይላል፦ “ከመልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ጋር በጉዞ ላይ ሳለን መልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ውዱእ አደረጉ፤እግራቸው ጋር ሲደርሱ ኹፋቸውን ላወልቅ ዝቅ አልኩ። እሳቸውም፦ “ተዋቸው(አታውልቃቸው) ሙሉ ጠሃራ ካደረግኩ በኋላ ነው ያጠለቅኳቸው።” ካሉኝ በኋላ በኹፋቸው ላይ አበሱ።

ስለዚህም አንድ  ሰው ያለ ጠሃራ ኹፍን ካደረገ ውዱእ ማድረግ ሲፈልግ አውልቆ እግሮቹን ማጠብ ይኖርበታል። ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ላለማውለቃቸው ምክንያት ያደረጉት ሙሉ ጠሃራ ማድረጋቸውን ነበር።

ሁለተኛው መስፈርት፦ ከሸሪዓው በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ መሆን አለበት። እርሱም፤ (ለሙቂም) በሀገሩ ተቀማጭ ለሆነ አንድ ቀን ከነለሊቱ ሲሆን (ለሙሳፊር) ለመንገደኛ ደግሞ ሦስት ቀን ከነለሊቱ  ማበስ ይችላልነ። ማበስ መቆጠር የሚጀምረው ውዱእን አጥፍቶ መጀመሪያ ካበሰበት ሰዓት ጀምሮ እስከ ማብቂያ ጊዜ ድረስ ይቀጥላል። መጀመሪያ ሳያብስ ያለፈው ጊዜ አይቆጠርም ሁለት ወይም ሦስት ቀን ውዱእ ሳያጠፋ ኹፍን ሲያብስ ባደረገው ውዱእ ላይ ከቆየ ይህ ጊዜ አይቆጠርበትም። መቆጠር የሚጀምረው ውዱእን አጥፍቶ ካበሰበት ሰዓት እስከሚያበቃበት ሰዓት ብቻ ይሆናል።

ለምሳሌ፦ አንድ ሰው እሑድ እለት ለፈጅር ውዱእ ካደረገ በኋላ ካልሲ ወይም ኹፍ ቢለብስ ውዱእን ሳያጠፋ እስከ ኢሻ ቆየና ኢሻ ሰግዶ ተኛ፤ ከዚያም ሰኞ እለት ፈጅር ተነስቶ ውዱእ አደርጎ ኹፍ ላይ ቢያብስ የማበሻ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ሰኞ ፈጅር ጀምሮ ይሆናል።ምክንያቱም ውዱእን ካጠፋ በኋላ መጀመሪያ ማበስ የጀመረው በዚህ እለት ነውና። ማብቂያውም ከላይ በጠቀስነው የጊዜ ገደብ ጊዜው ሲያበቃ አብሮ ይጠናቀቃል።

ሦስተኛው መስፈርት፦ ኹፍ የሚታበሰው ከትንሹ ሐደስ እንጂ ከጀናባ አይደልም።ሰውዬው ጀናባ ላይ ከሆነ በኹ  ላይ ማበስ አይችልም፤ እንዲያውም ኹፉን በማውለቅ መላ አካሉን መታጠብ ይኖርበታል። ሠፍዋን ኢብኑ ዓሳል ረዲየላሁ ዐንሁ ያስተላለፉት ሐዲስ ሲባል። እንዲህ ይላል፦ “መልክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ጉዞ  ላይ ስንሆን ለሦስት ቀናት ከነለሌታቸው ኹፋችን  እንዳናወልቅ አዘውናል። ከጀናባ ሲቀር፤ ከሽንት እና ከሰገራ ግን እንድናወልቅ አያዙንም ነበር።” በሰሒሁ ሙስሊም ከዓሊይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተዘግቦ በመጣው ትክክለኛ ሐዲስ መሰረት መልክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ኩፍ ላይ ለማበስ የጊዜ ገደብ አስቀምጠዋል። አንድ ቀን ከነለሌቱ ለተቀማጭ ሦስት ቀን የጊዜ ገደብ አስቀምጠዋል።

ኹፍ ላይ ለማበስ እነዚህ ሦስት መስፈርቶች መሟላታቸው የግዴታ ነው። ሌሎች መስፈርቶች ያሉ ሲሆን መስፈርቶችም ላይ ዑለማዎች ተለያይተዋል። ሆኖም ሸሪዓዊ አሕካሞች ከሚገነቡት መርሆ መካከል አንዱ፦ አንድ ነገር ላይ መረጃ እስካልመጣበት ድረስ መሰረቱ ከመስፈርት፣ከግዴታ፣ከከልካይ ተጠያቂነት ነፃ መሆን ነው




Share

ወቅታዊ