ጥያቄ(67): አንድ ሰው ላዩ ላይ ነጃሳ ቢኖርና ማስወገድ ባይችል ተየሙም ማድረግ አይፈቀድለትም ማለት ነው?
መልስ:
አዎን። አንድ ሰው ላይ ነጃሳ ቢኖርበትና ማስወገድ ባይችል እንደ ችሎታው መስገድ ይኖርበታል፤ በአቅሙ ልክ በመፋቅና በመሳሰሉት መንገዶች ነጃሳውን መቀነስ ይኖርበታል። እንበልና ለምሳሌ ልብሱን አውልቆ ሌላ ልብስ መቀየር ከቻለ አውልቆ ሌላን ልብስ ለብሶ ሀፍረቱን መሸፈን ይኖርበታል።