Back to Top
እምነት እንደሚጨምርና እንደሚቀንስ ያላረጋገጡ ሰዎች ምን አይነት ብያኔ ይሰጣቸዋል?

ጥያቄ(29): እምነት እንደሚጨምርና እንደሚቀንስ ያላረጋገጡ ሰዎች ምን አይነት ብያኔ ይሰጣቸዋል?
መልስ:

ይህ ሰው ኢማን (እምነት) ላይ ከሚያስተባብል ሰው ይመደባል። ይህን ነገር ውሸት ነው በሚል ከማስተባበል አንፃር ከሆነ ቁርአን ላይ የመጣ ነገር እንዳስተባበለ ተቆጥሮ ካፊር የሚል ብያኔ ይሰጠዋል።  ይህን ያለው ከተእዊል ተነስቶ ከሆነ ተእዊል ደግሞ ብዙ ደረጃዎች ስላሉት ወደ ኩፍር ደረጃ ሊደርስም ላይደርስም ይችላል። እምነት ይጨምራል፤ ይቀንሳል አልልም የሚል ሰው እንደ ተእዊሉ አይነት ታይቶ ብያኔ ይሰጠዋል።




Share

ወቅታዊ