ጥያቄ(18): አንድ ሰው ስለ ኢማን ሲጠየቅ ማለት ያለበት ኢማን ማለት በውስጡ የሚጠቁማቸውን መልክቶች መቀበልና መፈፀምን ያቀፈ ማመንና ማረጋገጥ ነው ብሎ ነው መመለስ ያለበት ወይስ መልክተኛው ለጂብሪል እንደመለሱለት
በአላህ መኖር ጌትነት አምላክነት፤ በመላክት መኖር፤ በመጽሃፍት መወረድ እና መልክተኞች መላክ ማመን … ነው ብሎ ነው መመለስ ያለበት?
መልስ:
ኢማን ማለት በውስጡ የሚጠቁማቸውን መልዕክቶች መቀበልና መፈፀም ነው ብለን እንመልሳለን ነገርግን ጠያቂው እነዚህን ነገሮች በዝርዝር እንዲነገረው የሚሻ ከሆነ ኢማን ማለት በአላህ ማመን፤ በመጽሓፍት መወረድ ማመን፤በመላኢካ ማመን… ብለን እንመልስለታለን። እነዚህ የዘረዘርናቸው የእምነት አካሎች በሙሉ የዲኑ መልክት ሙሉ ለሙሉ ያካተቱ ናቸው።