ጥያቄ(13): የላ ኢላህ ኢለሏህ ትርጉም እያየን ነበር ሙሀመዱ ረሱሉላህ ማለት ደግሞ ምን ማለት ነው?
መልስ:
ሙሀመዱ ረሱሉላህ ማለት ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲላህ አልቁረይሺ አልሃሺሚይ ለፍጥረታት በሙሉ ለሰዎች እና ለጂኖች መልክተኛ መሆናቸውን በልብ ማመንና በዐንደበት ማረጋገጥ ማለት ነው። አላህ እንዳለው፦
«እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደናንተ ወደሁላችሁም የአላህ መልክተኛ ነኝ፡፡ (እርሱም) ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ የኾነ ነው፡፡ እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ያደርጋል፡፡ ይገድላልም፡፡ በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ ነቢይ በኾነው መልክተኛው እመኑ፡፡ ቅንንም መንገድ ትመሩ ዘንድ ተከተሉት፡፡» [አልአዕራፍ:158]
የዚህ የምስክር ቃል በተዘዋዋሪ ግዴታ የሚያስደርገው ነገር እነሆ፦ መልክተኛው የተናገሩትን እውነት ብሎ መቀበል፤ያዘዙትን መታዘዝ፤የከለከሉትን መከልከል፤በርሳቸው ሸሪዓ ብቻ አምልኮትን መፈፀም። በተጨማሪም መልክተኛው አንድም የፈጣሪነት መብት አላቸው፤ አምልኮት ይገባቸው እና ፍጥረተ ዓለሙ ላይ ያስተናብራሉ ብሎ አለማመን። እንዲያውም መልክተኛው ባርያ እንጂ አይመለኩም። የማይስተባበሉ መልክተኛ ናቸው። አላህ በሻው ነገር ቢሆን እንጂ። ለራሳቸውም ሆነ ለሌላው ጥቅምን ማስገኘትም ሆነ መከላከል አይችሉም2።
አላህ እንዳለው፦
መልክተኛው የታዘዘውን የሚከተል ባሪያ ነው። ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል
እንዲህም ይላል፦
ይህ ነው የላ ኢላህ ኢለሏህ ሙሐመደ ረሱሉሏህ መልዕክት። ከዚህም መልዕክት የምንረዳው መልክተኛውም ይሁን ከሳቸው በታች ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ፍጥረታት ከአምልኮ ዘርፎች አንዱም አይገባቸውም። አምልኮ ለአላህ እንጂ የለሌላ የማንም መብት አይደለምና። የመልክተኛው መብት ደግሞ አላህ የሰጣቸው ደረጃ ላይ ማስቀመጥ ብቻ ነው። እርሱም የአላህ ባሪያና መልክተኛ መሆናቸውን መመስከር።
2 በተጨማሪም መለዕክተኛው የሩቡቢያ እና የፍጥረተ አለሙን የማስተናበር መብት እንደሌላቸው፤ አምልኮም እንደማይገባቸው፤ እንዲያውም የሚያመልኩ እና የማያስተባብሉ ባሪያ መሆናቸውንናለራሳቸውም ሆነ ለሌላው አላህ ባሸው ነገር ቢሆን እንጂ ጥቅም ማስገኘትም ሆነ መከልከል እንደማይችሉ ማመን ያጠቃልላል።