ጥያቄ(105): ሰላትን የሚያበላሹ ነገሮች በጥቅሉ ቢዘረዝሩልን።
መልስ:
ሰላትን የሚያበላሹ ነገሮች ሁለት ነገሮች ላይ የሚሽከረከሩ ሲሆኑ ዋጂብን መተው አሊያም ሰላት ውስጥ የተከለከሉ ተግባሮችን መፈፀም ናቸው።
ሰላት ውስጥ ግዴታ (ዋጂብ) ነገሮችን መተው ለሚለው ምሳሌው፦ ሆን ብሎ ከሰላት ማዕዘናት ወይም መስፈርቶች አሊያም ዋጂባት መካከል አንዱን መተው ነው።
ሩክን (የሰላት ማዕዘን) መተው ለሚለው ማሳሌ፦ ሆን ብሎ ሩኩዕ ማድረግን መተው።
ሸርጥ (የሰላት መስፈርት) መተው ለሚለው ማሳሌ፦ ሆን ብሎ ሰላት መሃል ላይ ከቂብላ አቅጣጫ ወደ ሌላ አቅጣጫ መዞር።
ዋጂብ (የሰላት ዋጂብ) መተው ለሚለው ማሳሌ፦ ሆን ብሎ የመጀመሪያውን ተሸሁድ መተው ሲሆን ከሰላት ዋጂባት መካከል አንዱን ሆን ብሎ የተወ ሰላቱ ብልሹ ይሆናል። ይህ ዋጂብ ብለን የምንጠራው ነገር ሸርጥ ወይም ሩክን አሊያም ዋጂብ ሊሆን ይችላል።
ሰላት የሚበላሹ ነገሮች ከሚሽከረከርባቸው ነገሮች መካከል በሁለተኛ ደረጃ ተጠቃሽ የሚሆነው፤ሰላት ውስጥ የተከለከሉ ድርጊቶችን መፈፀም ሲሆን ምሳሌውም እንደሚከተለው ነው፤
ሰላት ውስጥ ሳለ ውዱእን ማጥፋት፣ወይም ከሰዎች ጋር ማውራት፣ወይም ድምፅ አውጥቶ መሳቅ፣ ወይም ደግሞ ማንኛውም ሰላት ውስጥ ሆን ብሎ ሰላት የሚያበላሹ ድርጊቶችን መፈፀም ይገኙበታል። በዚህን ጊዜ ሰላቱ ይበላሽበታል።