ጥያቄ (31): በዳይንና አመፀኛ አስመልክቶ ተቀራራቢ ወይም አንዱ ሌላውን የሚተካ ነገር እንደሆነ ጠቅሰውልናል፤ እርሱም በዳይ የሚለውን ሲገልፁ አላህ ካወረደው ውጭ የሚፈርደው የአላህ ህግ የበላይ መሆኑን ያውቃል ነገር ግን አንድን ሰው መበቀል ስለሚፈልግ የአላህን ህግ ትቶ በሌላ ይፈርዳል። ፋሲቅ(አመፀኛ) ደግሞ የአላህን ህግ ያውቃል፤የአላህ ህግ ትክክል መሆኑንም ይረዳል። ነገር ግን ለራሱ ስሜት ወይም ለርሱ ጥቅም ወይም የሌላ ሰው ዝንባሌን ለመግጠም ሲል አላህ ካወረደው ውጭ ይፈርዳል። ስለዚህም በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድ ነው?
2019-02-17