Back to Top
ከሰላት ማዕዘናት መካከል አንዱን በመርሳት ላይ ጥርጣሬ ቢገጥመው ምን ያድርግ?

ጥያቄ(98): ከሰላት ማዕዘናት መካከል አንዱን በመርሳት ላይ ጥርጣሬ ቢገጥመው ምን ያድርግ?
መልስ:

መርሳት ላይ ጥርጣሬ ያደረበት ሰው ከሦስት ሁኔታዎች የወጣ አይሆንም።

አንደኛው፡- ጥርጣሬው መሰረተ ቢስ ሊሆን ይችላል። ይህ ከሆነ ሰላቱ ላይ ምንም ተፅእኖ አያሳድርም።ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በመቁጠር ሰላቱን ይቀጥላል።

ሁለተኛው፦  ለእኛም ሆነ ለነሱ ይመራን ዘንድ አላህን እየተማፀንኩ ብዙ ወስዋስ (ጉትጎታ) የሚበዛባቸው ሰዎች ላይ እንደሚስተዋለው ግለሰቡ ከባህሪው ጥርጣሬ የሚያይልበት ሊሆን ይችላል። በዚህም ጊዜ ሰላቱ ውስጥ ክፍተት የተፈጠረ ስሜት ቢሰማውም እንኳ ለጥርጣሬው ቦታ ባለመስጠት ሰላቱን ሊቀጥል እና ሊያጠናቅቅ ይገባል።

ሦስተኛው፦ ሰላቱን ካጠናቀቀ በኋላ የሰላት ተግባር መተዉ ላይ ቢጠራጠር። እዚህም ጋ እርግጠኛ እስካልሆነ ለዚህ ጥርጣሬ ቦታና ግምት ሊሰጥ አይገባም።

ሰላት መሀከል ላይ ጥርጣሬ ቢመጣበት ዑለማዎች ይህን አስመልክቶ፤አንድ የሰላት ማዕዘን ላይ ጥርጣሬ ያደረበት ሰው እንደተወ ይቆጠራል። ይህ ግን ጥርጣሬው ሰላት መሃል ላይ ሲከሰትና የእውነት ወይም እርግጠኛ ጥርጣሬ እንጂ መሰረተ ቢስ የሆነ ጥርጣሬን እና ወስዋስን (ጉትጎታን) አይመለከትም። እንበልና! ሱጁድ እያደረገ ሳለ ሩኩዕ ማድረጉ ላይ ቢጠራጠር ሩኩዕ ማድረጉ ላይ ያለው ግምት ጠንካራ ካልሆነ በስተቀር ተነስተህ ሩኩዕ ማድረግ አለብህ እንለዋለን። ምክንያቱም ሩኩዕ በመሰረቱ እንዳላደረገ ይቆጠራል። ጥርጣሬው ሩኩዕ በማድረጉ ላይ ካመዘነ በዚህን ጊዜ ሩኩዕ እንዳደረገ ይቆጠራል። ሆኖም ካሰላመተ በኋላ ሱጁድ ማድረግ ይኖርበታል። በውነቱ ከሆነ “ሱጁድ ሰህው” በጣም ወሳኝና አሳሳቢ ጉዳይ ሲሆን አንድ ሰጋጅ የዚህን ህግጋትን ጠንቅቆ ማወቅ ይጠበቅበታል። በተለይም አሰጋጆች። በርካታ ሰዎች የሱጁድ ሰህው ህግጋትን አያውቅም ይህ ከነሱ የሚጠበቅ ተግባር አይደለም። እንዲያውም አላህ በመልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ ያወረዳቸውን ህግጋት አማኞች ሊያውቋቸው ይገባል።




Share

ወቅታዊ