Back to Top
አላህ መልካም ምንዳችሁን ይክፈላችሁና ከላይ ሩኩእ እና ሱጁድ ወይም ቂያም እንዲሁም በሁለቱ ሱጁዶች መካከል አቀማመጥ ላይ የእጆች አቀማመጥን ጠቅሰውልን ነበር። ሆኖም ሁለት እግሮችን አስመልክቶ ግን እንዴት መቆም እንዳለባቸው ሲጠቅሱ አልሰማንም። ብዙ ግዜ ሰጋጆች እግራቸውን ከትከሻቸው በላይ አስፋፍተው ሲቆሙ እንመለከታለን። ስለሆነም ትክክለኛው የእግሮች አቋቋም እንዴት እንደሆነ ቢገልፁልን።

ጥያቄ(95): አላህ መልካም ምንዳችሁን ይክፈላችሁና ከላይ ሩኩእ እና ሱጁድ ወይም ቂያም እንዲሁም በሁለቱ ሱጁዶች መካከል አቀማመጥ ላይ የእጆች አቀማመጥን ጠቅሰውልን ነበር። ሆኖም ሁለት እግሮችን አስመልክቶ ግን እንዴት መቆም እንዳለባቸው ሲጠቅሱ አልሰማንም። ብዙ ግዜ ሰጋጆች እግራቸውን ከትከሻቸው በላይ አስፋፍተው ሲቆሙ እንመለከታለን። ስለሆነም ትክክለኛው የእግሮች አቋቋም እንዴት እንደሆነ ቢገልፁልን።
መልስ:

ለሰላት በምንቆምበት ሰዓት የሁለት እግሮች አቋቋም ሊሆን የሚገባው እግሮችን ማጠጋጋት ወይም በጣም ማስፋፋት ሳይኖርበት መደበኛ አቋቋም ሊቆም ይገባል። ከዐብዱላሂ ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ሸርሁ ሱናህ ላይ እንተዘገበው ሩኩእ እና ቂያም በሚያደርጉበት ሰዓት እግራቸውን አያራራቁም እንዲሁም አያጠጋጉም ነበር።

ቁጭ ሲል እንዴት እግሮቹን እንዴት ማድረግ እንዳለበት አሳልፈናል። ሱጁድ በሚደረግበት ግዜ ግን ሁለት እግሮችን ሳያራርቅ ማገጣጠሙ በላጭ ነው። ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ በጨለማ በዳሰሳ መልክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እየፈለገች ሳለ እጇ የመልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሁለት እግሮች ላይ አረፈ። በዚያን ሰዓት እግራቸው ተገጠጥመው መሬት ላይ ተቸክለው ነበር። እንደሚታወቀው ሁለት እግሮች ተገጣጥመው ካልሆነ በስተቀር አንድ እጅ ሁለት እግሮች ላይ ሊያርፍ አይችልም። እንደዚሁም ኢብኑ ኹዘይማ በትክክለኛ ሰነድ እንደዘገቡት መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሱጁድ ሲያደርጉ ሁለት እግሯቸውን በማገጣጠም ይሰግዱ እንደ ነበር ተዘግቧል።

የሰላት አሰጋገድ ከማገባበዳችን በፊት አንድ ሰው ሰላቱን ከጨረሰ በኋላ ከመልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተዘግበው በመጣው መሰረት ዚክር ማድረግ ይኖርበታል። ምክንያቱም አላህ አዘወጀል በዚህ አዟልና።

“ሶላትንም በፈጸማችሁ ጊዜ ቆማችሁም ተቀምጣችሁም በጎኖቻችሁም ላይ ተጋድማችሁ አላህን አውሱ፡፡ በረጋችሁም ጊዜ ሶላትን (አሟልታችሁ) ስገዱ፡፡ ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት  የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡” [አኒሳእ:103]

ከነዚህ ዚክሮች መካከል ሦስቴ “አስተግፊሩላህ” ማለት፤ከዚያም “አላሁመ አንተ ሰላም ወሚንከ  ሰላም ተባረክተ ያ ዘልጀላሊ ወልኢክራም” ይላል። ከዚያም ሌሎች ከመልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ተዘግበው የመጡት ዚክሮች ያደርጋል። ከዚያም ሰላሳ ሶስት ግዜ “ተስቢሕ”(ሱብሃነላህ)፣ተክቢር(አላሁ አክበር) እና ተሕሚድ ያደርጋል። ከፈለገ እያንዳንዱን በተናጥል አሊያ ሁሉንም ባንድ ላይ ማለት ይችላል። ማለትም፦ ከፈለገ ሰላሳ ሦስት ግዜ ሱብሃነላሁ፣ወልሐምዱሊላህ ፣ወላሁ አክበር  ይላል። አሊያም በተነጠል ሱብሃነላህ፣ሱብሃነላህ፣ሱብሃነላህ ይላል። ከዚያም ሰላሳ ሦስት ግዜ አልሐምዱሊላህ፣ ሰላሳ ሦስት ግዜ አላሁ አክበር ይላል። ይህ ሁሉ ይቻላል። እንዲያውም ሌላኛው የዚክር አደራረግ ይቻላል። ይኸውም፤አስር ጊዜ ተስቢህ፣ተክቢር እና ተህሚድ ማድረግ ይችላል። እንዲሁም አራተኛ የዚክር  አደራረግ ማድረግ ይቻላል። እርሱም፦ ሀያ አምስት ግዜ ሱብሃነላህ፣ሀያ አምስት ግዜ አልሐምዱሊላ፣ ሀያ አምስት ግዜ  ላኢላሀ ኢለሏ ሀያ አምስት ግዜ፤ አላሁ አክበር፤ ማለት ይቻላል።

በጥቅሉ መልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰላት በኋላ  ያደርጉ የነበረውን ዚክር ያድርግ። ስለሆነም የሰው ልጅ “አላህን አውሱ።” የሚለውን የአላህ ቃል እንዲሁም የመልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሱና መከተል ሲባል ዚክር ማድረግ ይጠበቅበታል።

መስጂድ ውስጥ ከሆነ እነዚህ ዚክሮች ድምፁን ከፍ በማድረግ ማለቱ በላጭ ነው። በሰሂሁል ቡኻሪ ከኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ ተዘግቦ በመጣው መሰረት በመልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘመን ፈርድ ሰላቶች ከተጠናቀቁ በኋላ ሁሉም ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ዚክር ያደርጉ ነበር።

ስለዚህም ሰጋጆች በነቢዩ ዘመን የነበሩ ሰሓቦቹን እና መልክተኛውን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም አርዓያ በማድረግ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ዚክር ማድረግ ይኖርባቸዋል።

ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦

 “ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ተክቢር በማድረጋቸው የተነሳ ሰላት መጠናቀቁን እናውቅ ነበር።” ከፊል ዑለማዎች ድምፅ ዝግ በማድረግ ዚክርን ማድረግ ሱና ነው። ይላሉ። መልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም  ይህን ያደርጉ የነበረው ሌላውን ለማስተማር ነው የሚለው አባባል አላቸው ይህ አባባል ለጥናት እና ለውይይት መቅረብ ይኖርበታል። ምክንያቱም የመልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ተግባር እና አፈፃፀም መሰረቱ ያንን ተግባር መፈፀም ለሁሉም እንደሚቻል ነው የምንገነዘበው። እንደሚታወቀው መልክተኛው ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በዚክር ላይ ድምፃቸውን ከፍ ማድረግ ለሌላው የማይፈቀድ ተግባር ቢሆን ኖሮ  እነዚህን ዚክሮች ለህዝቦቹ ማስተማራቸው ብቻ በቂ ነበር። ስለሆነም ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ማስተማር አይጠበቅባቸውም። በተጨማሪም አንዴ ወይም ሁለት ያንን ነገር በማድረግ ማስተማር ይቻላል። ነገር ግን ዘወትር ሰላት ባጠናቀቁ ቁጥር ድምፃቸውን ከፍ ማድረጋቸው ዓላማው ማስተማር ሳይሆን ሁሉም ይህንን ማድረግ እንደሚችል ለማሳየት ነው።
Share

ወቅታዊ