Back to Top
ሁለተኛው የሰላት መስፈርት ከማገባደዳችን በፊት ልብሱ ላይ ቀዳዳ ካለ ሰላት ተቀባይነት አለው ወይስ የለውም የሚለው ጉዳይ ለውይይት ሊቀርብ ይገባል። ብለዋልና እንዴት ነው ለውይይት የሚቀርበው?

ጥያቄ(90): ሁለተኛው የሰላት መስፈርት ከማገባደዳችን በፊት ልብሱ ላይ ቀዳዳ ካለ ሰላት ተቀባይነት አለው ወይስ የለውም የሚለው ጉዳይ ለውይይት ሊቀርብ ይገባል። ብለዋልና እንዴት ነው ለውይይት የሚቀርበው?
መልስ:

ልብሱ ቀዳዳ ከሆነ ለውይይት ይቀርባል ሲባል የቀዳዳው ዓይነት ይወስነዋል። እንዲሁም ከሁለት ብልቶች አከባቢ ሲሆንና ታፋውና ዙሪያ ጫፍ አከባቢ ሲሆን እንዲሁም ከመቀመጫው በላይ ጀርባው ላይ ሲሆንና ከእንምብርት በላይ ሆድ አከባቢ ቢሆን። ያም ሆነ ይህ! ሀፍረት እንደ ቦታው ታይቶ  ከባድና ቀላል ሊባል ይችላል። ምናልባትም ይህ ጥያቄ  ብዙ ሰዎች በጋ ሲሆን የሚፈፅሙት ነገርን አስመልክቶ ማሳሰቢያ ወደ መስጠት ይወስደናል። ይኸውም በጋ ላይ አጫጭር ሱሪዎችን በመልበስ ከላይ ደግሞ የሰውነት ቆዳ የሚያሳዩ ልብሶችን በመልበስ የሚሰግዱ ሰዎች አሉ። ይህ ዓይነቱን አለባበስ በመልበስ የሚሰገድ ሰላት ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም ከጉልበት አንስቶ እስከ እምብርት ድረስ የማይሸፍን ልብስ ለብሶ መስገድ አይቻልም። ከላይ የሰውነቱን ቀለም የሚያሳይ ልብስ መልበስ መሸፈኑ ግዴታ የሆነውን ሀፍረትን እንደሸፈን አይቆጠርም። ሆኖም የሰውነት ቅርፁን ቢያሳይም ችግር የለውም። እንደዚያም ሆኖ ወፍራም በሆነ ቁጥር የተሻለ ነው።

ለምሳሌ፦ አንዳንድ ልብሶች ከውስጥ የለበስከውን የውስጥ ሱሪ ያሳያሉ። ሆኖም የሰውነት ቆዳ ቀለምን ግን ማየት አያስችሉም። ይህ አይነቱ ልብስ ለብሶ መስገድ ሰላት ተቀባይነት ይኖረዋል። ሆኖም ከላይ እንዳሳለፍነው ወፍራም በሆነ ቁጥር የተሻለ ነው።

ከሰላት መስፈርቶች መካከል ጠሃራ ይገኝበታል። እርሱም ከሐደስ እና ከነጃሳ ጠሃራ መሆን በሚል ለሁለት ይከፈላል።

መጀመሪያው ከሐደስ ጠሃራ መሆን፤

ሐደስ ሁለት አይነት ሲሆን ትልቁ ማለትም ትጥበት ግዴታ የሚያስደርግ እና ትንሹ ማለትም ውዱእን ግዴታ የሚያስደርግ ነው። ትጥበትና ውዱእን ግዴታ የሚስደርጉ ነገሮች እና ሰበቦቹ ምን ምን እንደሆኑ ከላይ ጠቅሰናል። እነሱም፦ ውዱእን የሚያበላሹና ገላን መታጠብ ግዴታ የሚያስደርጉ ነገሮች ሲሆን ዳግም እዚህ መጥቀሳችን አስፈላጊ አይደለም።

ሆኖም እዚህ ቦታ ላይ ርእሳችን የሚመለከተው ከሐደስ ጠሃራ መሆን ከሰላት መስፈርቶች አንዱ መሆኑን መጥቀሳችን ነው የሚያሳስበን ስለሆነም እንድንርቃቸው ከታዘዝንባቸው ትዕዛዞች ውስጥ ይካተታሉ። የእውቀት ባለቤቶች ዘንድ ከሚታወቁ መርሆዎች መካከል፤  በታዘዝንባቸው ነገሮች ላይ መርሳት ሆነ አለማወቅ እንደ ዑዝር (ምክንያት) ሆነው ሊቆጠሩ አይችሉም። ከዚህ መርህ በመነሳት አንድ ሰው ረስቶ ያለ ውዱእ ቢሰግድ ውዱእ በማድረግ ሰላቱን ዳግም መስገድ ይኖርበታል። ምክንያቱም እንዲፈፅመው የታዘዘውን ሳያሟላ በመስገዱ የተነሳ። ሆኖም ረስቶ ያለ ውዱእ በመስገዱ ወንጀል አይኖርበትም። አላህ አዘወጀለ እንዲህ ብሏልና ፦

“ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን፤ (አትቅጣን)፡፡ “ [አልበቀራ:186]

ሆኖም ሰላቱ ተቀባይነት የለውም። ሰላቱ እንደሰገደ አይቆጠርምና ዳግም መስገድ ይጠበቅበታል።

ብቻውን ሆነ ኢማምን ተከትሎ አሊያም ኢማም ሆኖ ሳለ በመርሳት ያለ ውዱእ ወይም ጀናባውን ሳይታጠብ የሰገደ በሙሉ ባስታወስ ጊዜ  ሰላቱን ዳግም መስገድ ይኖርበታል። ኢማም ከሆነ ከኋላው ያለውን ሰው የተቀረውን ሰላት እንዲያሟላ በማዘዝ ከሰላት መውጣት ይኖርበታል። ይህን ሳያደርግ ዝም ብሎ ከሰላት ከወጣ ሰጋጆቹ ከመሃላቸው አንዱን እንዲያሰግድ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ይህን ሳያደርጉ ቢቀር ሁሉም በግሉ ሰላቱን ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል። ሰላቱ በአዲስ መልኩ መጀመር በነሱ ላይ ግዴታ አይሆንም። ኢማማቸው ያለ ውዱእ እንዳሰገዳቸው በኋላ ላይ ቢያውቁም ዳግም መስገድ አይጠበቅባቸውም። ምክንያቱም ኢማሙ ውዱእ ይኑረው አይኑረው ባለማወቃቸው ለነርሱ ዑዝር አላቸው። እንደዚሁም ባለማወቅ ያለ ውዱእ ሰላት ቢሰግድ ማለትም የግመል ስጋ ያለበት ምግብ ቢቀርብለትና የግመል ስጋ በልቶ የግመል ስጋ መሆኑ ሳያውቅ ተነስቶ ውዱእ ሳያደርግ ከሰገደ በኋላ የበላው ስጋ የግመል ስጋ መሆኑ ቢያውቅ ውዱእ ማድረግና ሰላቱን ዳግም መስገድ አለበት። ሰላት በመስገዱ ግን ወንጀል የለበትም። ውዱእ እንደጠፋበት ባያውቅም ጠፍቶበታል። አላህ አዘወጀለ እንዲህ ይላል፦

 “ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን፤ (አትቅጣን)፡፡ “ [አልበቀራ:186]




Share

ወቅታዊ