ጥያቄ(9): የመጨረሻውን የተውሒድ ክፍል ማለትም ተውሒዱ አስማኢ ወሲፋት ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲያደርጉልን እንሻለን።
መልስ:
በእውነቱ ይህ የተውሒድ ክፍል ማለትም ተውሒዱ አስማኢ ወሲፋት በጣም አሳሳቢ ስለሆነ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባል። ምክንያቱም ሙስሊሙ ህዝብ ለብዙ አንጃዎች የተከፋፈለውም በዚሁ ርዕስ ላይ ነው። በአላህ ያመኑ፤ ሰለፎች እና እነሱን በመልካም የተከተሉ ወገኖች ሰዎች በተለያዩበትና ባልተግባቡበት ነገር ትክክለኛውን መንገድ በርሱ ፍቃድ ተመርተዋል። አላህ የሻውን ቀጥተኛውን ጎዳና ይመራል።
ለዚህ የተውሒድ ክፍል መርሆ የሚሆነንን ከላይ አሳልፈናል፤ እርሱም አላህ ለራሱ ያፀደቀውን ማፅደቅ ወይም መልክተኛው ለአላህ ያፀደቁትን ስምና ባህሪያትን በተገቢውና በሐቂቃው ያለ ተሕሪፍ ፤ተዕጢል፤ተክዪፍ እና ያለ ተምሲል ማፅደቅ። ለዚህ የሚሆነንን ከአላህ ስሞች መካከል ለምሳሌነት ከላይ አቅርበናል። ከባህሪያትም አንድ ምሳሌን የጠቀስን ሲሆን እርሱም ሁለት እጆች የሚለው ነው። ስሞችን አስመልክቶ አላህ እራሱን የሰየመበት ለእርሱ ስም አድርገን ማፅደቅ ግዴታ መሆኑን ጠቅሰናል። ስም በውስጡ የያዘውን ባህሪና ፍርድ ማፅደቅ ግዴታ ነው። ይህም ማለት ባህሪው የሚያሳድረው አዎንታዊ ተፅእኖ በሐቂቃው ያለ ተሕሪፍ ፤ተዕጢል፤ተክዪፍ እና ያለ ተምሲል ማፅደቅ እንደሚገባም ከላይ አሳልፈናል። ለዚህም ምሳሌ ሁለት እጆች የሚለውን በምሳሌነት ጠቅሰናል። አላህ ለራሱ ሁለት እጆችን አፅድቋል። ስለዚህም እነዚህን እጆች በተገቢው መልኩ በሐቂቃው ልናጸድቅ ይገባል። ነገር ግን እነዚህ ሁለት እጆች ከፍጥረታት እጆች ጋር ማመሳሰል አይገባም። በቀልባችንም ሆነ በምላሳችን ስለ ሁለቱ እጆች ዝርዝር መግለጫ መስጠት አይፈቀድም።ምክንያቱም ማመሳሰለ የአላህን ቃል እንደማስተባበል ይቆጠራል።
ተክዪፍ ማድረግ( ዝርዝር መግለጫ መስጠት) ደግሞ አላህ የከለከለውና ሐራም የሆነ ድርጊትን እንደመፈፀም ይቆጠራል። ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏልና።
ባህሪያትን አስመልክቶ ሁለተኛውን ምሳሌ እናክላለን። እርሱም አላህ ከአርሹ በላይ ከፍ ማለቱን አስመልክቶ አላህ “ኢስተዋ” (ከፍ አለ) በሚል ቁርኣኑ ውስጥ ሰባት ቦታዎች ላይ ተጠቅሷል። “ኢስተዋ” የሚለው ወደ ቋንቋዊ ትርጓሜው ስንመልሰው “ዓላ” በሚል ሐርፍ ከተደገፈ ከፍ ማለት እና ክፍታን ብቻ ነው የሚጠቁመው። ስለዚህም
የሚለው አንቀፅና መሰሎቹ ከዐርሹ ከፍ አለ የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል። መልክቱም አላህ ለርሱ በሚገባው መልኩና ፍፁም ለየት ባለ መልኩ ዐርሹ ላይ ከፍ ብሏል። በዚህ መልኩ “ዑልውን” ስናፀድቅ በሐቂቃው መሆን አለበት። አላህ ለርሱ በሚገባው መልኩ ዐርሹ ላይ ከፍ ብሏል። የሰው ልጅ ዙፋኑ ላይ ሲቀመጥ ወይም የጋማ ከብቶች ላይ አሊያም መርከብ ላይ ሲቀመጥ ካለው ሁኔታ ጋር ፈፅሞ አይመሳሰልም። ይህን በማስመልከት አላህ እንዲህ ብሏል። [ያም ዓይነቶችን ሁሉ የፈጠረ ለእናንተም ከመርከቦችና ከቤት እንስሳዎች የምትጋልቧቸውን ያደረገላችሁ ነው፡፡በጀርባዎቹ ላይ እንድትደላደሉ ከዚያም በርሱ ላይ የተደላደላችሁ ጊዜ የጌታችሁን ጸጋ እንድታስታውሱ፤ እንድትሉም፡-
ስለዚህም ፍጡር በአንድ ነገር ላይ ከፍ ማለት ወይም መደላደል ከአላህ ከፍ ማለት ጋር ፈፅሞ አይመሳሰልም። ምክንያቱም አላህን በየትኛውም ባህሪው የሚመስለው የለምና።
“አላህ ከዐርሹ በላይ ከፍ አለ።” የሚለውን አንቀፅ “አላህ በስልጣኑ ዐርሽን ተቆጣጠረ።” ብሎ የተረጎመ ከባድ ስህተት ላይ ወድቋል። ምክንያቱም ይህ የአላህ ቃል ከቦታው ማዛነፍ ውስጥ የሚካተት ነውና። ሰሓቦችና እነሱን በመልካም የተከተሉ ትውልድን በሙሉ የጣሰ አመለካከት ነው። ከንደገናም አንድ አማኝ አፉን አውጥቶ ስለ አላህ መናገር የሚከብድ ለርሱ(ለአላህ) የማይገባ መጥፎ መልክትን በተዘዋዋሪ ያስጨብጣል። የተከበረው ቁርኣን ያለምንም ጥርጥር በዐረብኛ ቋንቋ ነው የተወረደው። አላህ እንዳለው፦
“በሆነ ነገር ላይ ኢስቲዋእ አደረገ።” የሚለው በዐረብኛው ዘይቤ የሚያስፈርደው ትርጉም ፦ ከፍ ማለት፤መደላደል የመሳሰሉትን ትርጓሜ ነው እንዲያውም ትርጓሜው ከቃሉ ጋር እጅግ የሚጣጣም ነው።
“አላህ ከዐርሹ በላይ ከፍ አለ።” ማለት ከፍጥረታት ፍፁም በተለየ መልኩ ለልቅናውና ለክብር በሚገባ መልኩ ከፍ አለ የሚለውን ትርጓሜ ይሰጠናል። ነገር ግን በስልጣኑ ተቆጣጠረ ብለን ከተረጎምነው የአላህ ቃልን ከቦታው አዛባን ማለት ነው። ምክንያቱም ትርጉሙን ቁርኣን ከወረደበትን ከዐረብኛ ቋንቋ አውጥተንዋልና። ከንደገናም ሰለፎችና እነሱን በመልካም የተከተሉ ትውልዶች አላህ ከዐርሹ በላይ ከፍ አለ በሚለው ስምምነት አለ።ከነርሱ ይህን የሚቃረን አንድም ፊደል አልተገኘም። በቁርኣንና በሐዲስ አንድ ቃል መጥቶ ከሰለፎቹ ያንን ቃል የሚቃረን ነገር ካልመጣ ሰለፎቹ ቃሉን እንደመጣ ተቀብለው መልክቱን አምነውበታል የሚለውን ያሳየናል። ምንልባትም አንድ ሰው “ሰለፎች ኢስተዋ የሚለውን ቃል አስመልክቶ ከፍ አለ ብለው የተረጎሙበት ግልፅ መረጃ አላችሁን? በማለት ጥያቄ ሊያቀርብ ይችል ይሆናል። “አዎን። ይህን የሚጠቁም ትርጉም ከሰለፎች መጥቷል” የሚል ይሆናል መልሳችን።በዚህ መልኩ በግልፅ ከነርሱ አልመጣም ቢባል እንኳ የቁርኣንና የሐዲስ መልክቶች ዐረብኛ ቋንቋ ከሚያስጨብጠው መልክት ጋር በዛሂሩ መተርጎም ይኖርበታል።
ኢስተዋ የሚለውን በስልጣኑ ተደላደለ ብለን የምንተረጉም ከሆነ ብልሹ መልክትን በተዘዋዋሪ ያስይዘናል። እስኪ ይህን የቁርኣን አንቀፅ እናስተውለው ፦
“ኢስተዋ” የሚለውን ዐርሽን በስልጣኑ ተቆጣጠረ ብለን ብንተረጉመው አላህ ሰማያትና ምድርን ከመፍጠሩ በፊትና እየፈጠረ ባለበትም ሰዓት ዐርሽ ከአላህ ቁጥጥር ውጭ ነበር የሚለውን መጥፎ መልክትን ያስጨብጠናል።ከንደገናም እንዲህ የምንል ከሆነ በውስጠ ታዋቂ አሊያም በግልፅ አላህ ምድርን ተቆጣጠረ፤ተራራውን ወዘተ… ተቆጣጠረ። የሚል ከአላህ ቃል ፈፅሞ የማይጠበቅ የተንዛዛ መልክትን ያስይዛል። ይህ ደግሞ ለአላህ የማይገባ ባጢል መልክትን ያስጨብጠናል። ከዚህም ትንታኔ ግልፅ የሚሆንልን ነገር ቢኖር ኢስቲዋን በስልጣኑ ዐርሽን ተቆጣጠረ ብለን የምንተረጉም ከሆነ ሁለት ክልክል የሆኑ ተግባሮችን ፈፅመናል ማለት ነው።
አንደኛው: የአላህ ቃል ትርጉሙን ማዛባት።
ሁለተኛው: አላህን በማይገባው መልኩ እየገለፅነው ማለት ነው።