ጥያቄ(82): አንዲት ሴት ከወሊድ ደም ከጠራች አሊያም ከመሰረቱ ደሙ የማይፈሳት ሴት ከሆነች የወሊድ ደም ላይ እንዳለች ሴት ትቆጠራለችን? መልስ:
በወሊድ ግዜ ደም የማይፈሳት ከሆነች የወሊድ ደም ላይ እንዳለች ሴት አትቆጠርም። ምንም ነገር እሷ ላይ ግዴታ የሚሆን ነገር የለም። ትጥበት ግዴታ አይሆንባትም እንዲሁ ሰላትም ሆነ ጾም በርሷ ላይ ሐራም አይሆንም።