Back to Top
ትጥበትን ግዴታ የሚያደርጉ ነገሮች ውዱእንም ያበላሻሉን? ወይስ አያበላሹም?

ጥያቄ(77): ትጥበትን ግዴታ የሚያደርጉ ነገሮች ውዱእንም ያበላሻሉን? ወይስ አያበላሹም?
መልስ:

ሊቃውንቶቻችን አላህ ይዘንላቸውና እነሱ ዘንድ በስፋት የሚታወቀው መርህ፤ ትጥበት ግዴታ ያደረገ ውዱእንም ግዴታ ያስደርጋል የሚል ነው። ሞት ሲቀር፡ከዚህ መርህ በመነሳት ትጥበትን ግዴታ  ከሚያስደርጉ ነገሮች ሊታጠብ ሲፈልግ አብሮ ውዱእን መነየት ይኖርበታል። ወይ ውዱእን ማድረግ አሊያ ግን ሁለቱንም ኒያ ካሰበ ትጥበቱ ያብቃቃዋል። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ለትልቁ ሐደስ(ጀናባ) የተነየተው ኒያህ ለትንሹ ሐደስ (ውዱእ) ያብቃቃል ወደሚለው አቋም ያመራሉ።

ምክንያቱም አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ)  እንዲህ ይላልና፦ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሶላት በቆማችሁ (ለመቆም ባሰባችሁ) ጊዜ ፊቶቻችሁን፣ እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡ ራሶቻችሁንም (በውሃ) አብሱ፡፡ እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)፡፡ (ሴት ጋር በመገናኘት ወይም በሌላ ምክንያት «ጀናባ») ብትኾኑ (ገላችሁን) ታጠቡ፡፡ በሽተኞች ወይም …. “ [አልማኢዳ ፡ 6]

አላህ እዚህ ቦ ታ ላይ ጀናባ አስመልክቶ መጥራትን ወይም መታጠብን እንጂ ሌላ አልጠቀሰም።ውዱእን አልጠቀሰም። መልክተኛውም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ቡኻሪ ዒምራን ኢብኑ ሑሰይን ጠቅሰው በዘገቡት ረጅም ሐዲስ ላይ አንድ ሰው ገላውን እንዲታጠብ ውሃ ሲያቀብሉት ፦ “ሂድና እራስህ ላይ አፍስ።”አሉት። ውዱእን አድርግ አላሉትም።

እዚህ  ላይ ሸይኩል ኢስላም የያዙት አቋም ለሐቅ የቀረበ ነው። ይኸውም ትልቁን ሐደሰ የነየተ ትንሹንም ሐደስለማስወገድ ነይቷል የሚለው ነው። ከዚህም በመነሳት ትጥበትን ግዴታ የሚያደርጉ ነገሮች ውዱእን ከሚያፈርሱ ነገሮች የተለዩ  ናቸው።
Share

ወቅታዊ