Back to Top
የውዱእ አደራረግና አፈፃፀሙ እንዴት ነው?

ጥያቄ(68): የውዱእ አደራረግና አፈፃፀሙ እንዴት ነው?
መልስ:

ሸሪዓዊ የውዱእ አደራረግ ሁለት አይነት ነው፦

የመጀመሪው አይነት፡ ዋጂብ የሆነውና ያለርሱ ውዱእ ተቀባይነት የሌለው የውዱእ አደራረግ ሲሆን በሚቀጥለው የቁርኣን አንቀፅ ተጠቅሶ እናገኘዋለን።

"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሶላት በቆማችሁ (ለመቆም ባሰባችሁ) ጊዜ ፊቶቻችሁን፣ እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡ ራሶቻችሁንም (በውሃ) አብሱ፡፡ እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)፡፡” [አል ማኢዳ ፡6]

እርሱም ፊትን አንዴ ማጠብ ፊትን ከማጠብ ውስጥ ከሚካተተው መካከል መጉመጥመጥ እና  ውሃን በአንፍጫ መሳብ ፣ እጅን እስከ ክርን ማጠብ ማለትም ከጣቶች ጫፍ ተነስቶ እስከ ክርን ድረስ ማጠብ፣ራስን አንዴ ማበስ፣ ከራስ ክፍል ውስጥ ሁለት ጆሮችን ማበስ ይካተታል። ሁለት እግሮች እስከ ቁርጭምጭሚት አንዴ ማጠብ። ግዴታ የሆነው የውዱዕ አደራረግ  እና አፈፃፀም ይህን ይመስላል።

ሁለተኛው የውዱእ አደራረግ ሙስተሓብ የሆነ የውዱእ አደራረግ ሲሆን በአላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ)  በመታገዝ በቅደም ተከተል እንጠቅሳለን። እነርሱም ውዱእ ሲጀምር ቢስሚላህ ብሎ መጀመር፣መዳፎችን ሦስት ጊዜ ማጠብ፣ከዚያም ሦስቴ ውሃ በመዝገን  ሦስቴ መጉመጥመጥ ፣ሦስቴ በአፍንጫ ውሃ መሳብ፣ከዚያም ሦስቴ ፊትን ማጠብ፣ከዚያም ሁለት እጆችን ሦስቴ  እስከ ክርን ማጠብ፣መጀመሪያ ቀኝን ከዚያም ግራን ማጠብ፣ ከዚያም ራስ ቅልን አንዴ ማበስ፣ከግንባር ጀምሮ እስከ ኋላ ፀጉር መብቀያ ካበሳ በኋላ ዳግም ከጀመረበት ላይ ይመልሳል። ከዚያም ራስን ያብሳል።

አመልካች ጣቶቹን የጆሮን ውስጠኛውን ክፍል ሲያብሱ በአውራ ጣቶቹ ደግሞ የጆሮን ላይኛውን ክፍል ያብሳል። ከዚያም እግሮቹን እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ ሦስቴ ያጥባል። መጀመሪያ ቀኝ እግሩን በማስቀደም ከዚያም ግራ እግርን ያጥባል። ከዚያም ሲያጠናቅቅ አሽሃዱ አን ላኢላሀ  ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከለሁ ወአሽሀዱ አነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ፣አላሁመ ኢጅዐልኒ ሚ ነ ተዋቢን ወጅዐልኒ ሚነል ሙተጠሂሪን ይህን ካደረገ ስምንቱ የጀነት በሮች ተከፍቶ በፈለገው በር እንዲገባ ይደረጋል።ዑመር ረዲየላሁ ባስተላለፉት ሐዲስ ከመልክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) በዚህ መልኩ በትክክለኛ ሰነድ ተዘግቦ ይገኛል።
Share

ወቅታዊ