ጥያቄ(63): ለነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ሩሕ ቁርኣን መቅራት ወይም ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ቀብር ዘንድ ፋቲሓ መቅራት አደራ የሚሉ ሰዎች አሉ ይህን አስመልክቶ ምን ይሉናል?
መልስ:
ይህን ወሲያህ (አደራ) መፈፀም ግዴታ አይደለም። ምክንያቱም በሸሪዓው የታዘዘ ተግባር አይደልምና። መልዕክተኛውም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) አንድንም ሰው ዒባዳ ሰርቶ ዒባዳውን ለመልክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲያደርግ ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) አልደነገጉም። ይህ ተግባር በሸሪዓው የተደነገገ ቢሆን ኖሮ በዚህ ተግባር ሰሓቦቹ (ረ.ዐ.) በቀደሙን ነበር። ምክንያቱም መልክተኛው ይህ አይነቱ ተግባር አያስፈልጋቸውምና። ማንኛውም ሰው አንድ ተግባር አይፈፅምም ለመልክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ከዛ ስራ መልካም ምንዳ ድርሻ ቢኖራቸው እንጂ። ምክንያቱም ያን መልካም ስራ እንዲሰራ የጠቆሙት እነርሱ ናቸውና። መልክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም )“መልካም ስራን የጠቆመ እንደተገበረው ይቆጠራል።” ይህ ማለትም ለነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ሩሕ ፋትሃን መቅራት ዋጋ የሌለው ጨዋታ ነው እና ከሰለፎችም ተዘግቦ ያልመጣ ከቢድዓ ተግባሮች መካከል አንዱ ነው። ልክ እንደዚሁ ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ቀብር ዘንድ ፋቲሓን መቅራት አለብህ ቢሉህ ይህን ወሲያ (ኑዛዜ) መፈፀም አይጠበቅብህም። ምክንያቱም አንድን ዒባዳ በሸሪዓው በቦታ ተገድቦ ሳይመጣ በቦታ መገደብ ቢድዓ ነው። መልክተኛውን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) መከተል በሚለው ጥናት ስር እንደተጠቀሰው ሙታበዓህ “መልክተኛውን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) መከተል” ዒባዳ በስድስት ነገሮች ካልተገጣጠመ ዒባዳ አይሰኝም። እነሱም፦ ሰበቡ መገኘት፣አይነቱ፣መጠኑ፣አፈጻጸሙ፣ቦታ እና ወቅቱ የተገደበ ነው።