ጥያቄ(60): ሰለፎች ቁርኣን አስመልክቶ ያላቸው እምነት ምንድን ናው?
መልስ:
ሰለፎች ቁርኣንን አስመልክቶ ያላቸው እምነት ልክ እንደ ተቀሩት የአላህ ባህሪያት እና ስሞች ነው። እምነታቸውም በቁርኣንና በመልዕክተኛው ሐዲስ ላይ የተመሰረተ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው ቁርኣንን አላህ ቃሉ ወይም ንግግሩ እንደሆነ ገልፆታል። ከርሱም ዘንድ የተወረደ ነው። ስለዚህም ይህን አስመልክቶ አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ ) እንዲህ ይላል፦
ቁርኣን ቃሉም ትርጉም የአላህ ነው። በሐቂቃው ተናግሮበታል። ለታማኙ ጂብሪል ምላሱ ላይ አደረገለት። ጂብሪል ደግሞ ግልፅ በሆነ ዓረብኛ ቋንቋ ዓለማትን ያስጠነቅቅ ዘንድ በመልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ቀልብ ላይ አወረደው። ሰለፎች ቁርኣን ከአላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ) ዘንድ በሃያ ሦስት ዓመት ውስጥ የርሱ ጥበብ እንደሚያስፈረደው ተከፋፍ እንደወረደ ያምናሉ።
ከዚያም በመቀጠል ቁርኣን አወራረዱ በሰበብና ያለሰበብ ይወርዳል። ይህም ማለት አንዳንድ የቁርኣን አንቀፆች ወይም ሱራዎች እንዲወርዱ የሚያደርጋቸው ሰበቦች ይኖራሉ። ሌላው ደግም ያለምንም ሰበብ ይወርዳል።አንዳንዱ ደግሞ መልዕክተኛውና ባልደረቦቻቸው ከኖሩበት ዘመን ቀደም ብሎ ያለውን የሚተርክ ይሆናል። አንዳንድ አንቀጾች ደግሞ ከጅማሪው የአላህ ህግጋትን ሊያብራሩ ይወርዳሉ።ይህን አስመልክቶ የእውቀት ባለቤቶች እንደጠቀሱት።
ሰለፎች ቁርኣን ጅምሩ ከአላህ ሲሆን ወደሱም ይመለሳል ይላሉ። ሰለፎች ቁርኣን ላይ ያላቸው እምነት ይህን ይመስላል።አላህ ቁርኣኑን አስመልክቶ በከባባድ መገለጫዎች እንደገለፀው ከሁላችንም የሚሰወር አይደለም። ቁርኣኑ ሐኪም (ጥበበኛው)፣ ከሪም (ቸር)፣ መጂድ (የላቀው) ሲል ይገልፀዋል። በዚህ መልኩ ቃሉን አላህ ይገለፀዋል።ቁርኣንን አጥብቆ ካልያዘው ሰው ይልቅ በደንብ አጥብቆ ለያዘው፣በመልዕክቱም ውጫዊና ውስጣዊ ተግባሩን በቁርኣን ያነፀ እነዚህ ባህሪያት ለርሱ የተገቡ ናቸው። ማለትም ልቅናን ፣ታላቅነትን፣ጥበብን፣አሸናፊነትንና ስልጣንን አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ) ለርሱ ያደርግለታል።ሙስሊሞች የአላህን ውዴታ እንዲያገኙ፣የበላይነት ደስታና ልቅና እንዲኖራቸው በምዕራቡና በምስራቁ ዓለም የበላይ እንዲሆኑ ስል ከዚህ መድረክ መላው ሙስሊምን መሪም ሆነ ተመሪ፣ዑለማእም ሆነ ተራውና ሰፊው ማህበረሰብን ውስጣቸውንም ሆነ ውጫቸውን በቁርኣን በማነፅ ቁርኣንን አጥብቀው ይይዙ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ።