Back to Top
ተቀባይነቱ የፀደቀ እና ውድቅ የሆነው የሸፋዓ አይነት ምን ምን ናቸው?
   ዐቂዳ (እምነት ነክ ጉዳዮች)        ምልጃ

ተቀባይነቱ የፀደቀ እና ውድቅ የሆነው የሸፋዓ አይነት


ጥያቄ(59): ተቀባይነቱ የፀደቀ እና ውድቅ የሆነው የሸፋዓ አይነት ምን ምን ናቸው?
መልስ:

ሸፋዓ የሚለው ቃል “ሸፍዕ” (ጥንድ) ከሚለው ዓረብኛ ስርወ ቃል የተወሰደ ነው። እርሱም የነጠላ ተቃራኒ ነው። ነጠላ የሆነ ነገር ጥንድ ማድረግ ሸፍዕ ይባላል። ለምሳሌ አንድን ሁለት ማድረግ፣ሦስትን አራት ማድረግ እና የመሳሰለው ስሌት በቋንቋዊ አገባብ ሸፍዕ ይባላል። 

በኢስጢላሂዊው ትርጓሜው ደግሞ ጥቅም ያገኝ ዘንድ ወይም ጉዳትን እንዳይደርስበት ለሆነ አካል ጣልቃ መግባት ሸፋዓ ይባላል።

ሸፈዓ ሁለት አይነት ሲሆን ትክክለኛ እና የፀደቀ ሸፋዓ እና ከንቱ  እና ለባለቤቱ ጠቃሚ ያልሆነ የሸፋዓ አይነት ይባላሉ።

ትክክለኛ እና የፀደቀ የሸፋዓ አይነት፡ አላህ በቁርኣኑ መልዕክተኛው በሐዲሳቸው ያፀደቁት የሸፋዓ አይነት ሲሆን ለተውሒድ ባለቤቶች እና አምልኮታቸውን ለአላህ ፍፁም አድርገው ላደረሱ  ሰዎች ብቻ ነው የሚገባው። ምክንያቱም አቡ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ መልዕክተኛውን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) የእርሶን ሸፋዓ በማግኘት እድለኛ የሚሆነው ማነው ብለው ሲጠይቋቸው፦ መልዕክተኛውም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ፦ “ላ ኢላሀ ኢለ ሏህ” ከአላህ ውጭ በእውነት የሚገዙት አምላክ የለም የሚለውን  ጥርት አድርጎ ከልቡ የተናገረ ነው። በማለት መለሱለት።

ትክክለኛው እና የፀደቀው የሸፋዓ አይነት ሦስት መስፈርቶች አሉት። 

የመጀመሪያው መስፈርት አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ) አማላጅን  ስራውንና ተግባሩን  ሊወድለት ይገባል። ሁለተኛው መስፈርት ደግሞ አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ) ተማላጅን ስራውንና ተግባሩን  ሊወድለት ይገባል። ሦስተኛው ደግሞ አማላጅ ሊያማልድ ዘንድ ከአላህ ፍቃድ ማግኘት ይኖርበታል። እነዚህ መስፈርቶች በሙሉ በቀጣዩ  አንቀፀ ተጠቅለለው ተጠቅሰዋል።

“በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች (ሊማለዱለት) ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡” [አነጅም:26]
በዝርዝር ደግሞ  በቀጣዮቹ አንቀፅ ተጠቅሰው ይገኛሉ። “ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢሆን እንጅ የሚያማልድ ማነው? “ [አልበቀራ:255]
አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ)  እንዲህ ይላል ፦“በዚያ ቀን ለእርሱ አልረሕማን የፈቀደለትንና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሰው ቢኾን እንጅ ምልጃ (አንድንም) አትጠቅምም፡፡” [ጧሃ፡109]
እንዲህም ይላል፦ “(አላህ) ለወደደው ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡”[አል አንቢያ:28]

ሸፋዓው ይፀድቅ ዘንድ እነዚህ መስፈርቶች መሟላት ይኖርባቸዋል።

ከዚህ መሰረት በመነሳት ሁለተኛው ማለትም ተቀባይነት የሌለው የሸፋዓ አይነት ምን እንደሆነ  እናውቃለን። ሙሽሪኮች አማልክቶቻቸው አላህ ዘንድ ያቃርቡናል ብለው በመሞገት እነሱን ይማፀናሉ። ይህ አይነቱ ምልጃ ለነሱ አይጠቅማቸውም፦

“የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፡፡” [ሙደሲር:48]

ምክንያቱም አላህ ሽርካቸውን ለነሱ አይወድላቸውም። ይህን   የሸፋዓ ዓይነት በፍፁም አላህ ሊፈቅድላቸው አይችልም። ምክንያቱም እርሱ ለወደደው በስተቀር ሸፋዓ የለምና።አላህ ደግሞ  ለባሮቹ ኩፍርን (ክህደትን) አይወድም። በምድር ማበላሸትንም አይወድም። ሙሽሪኮች ከአላህ ውጭ የሚያመልኳቸውን አማልክት ያማልዱናል በማለት በነሱ ላይ ልባቸውን ማንጠልጠላቸው ከንቱ እና ጠቃሚ ያልሆነ መንጠልጠል ነው። እንዲያውም አጋሪያን በዚህ ተግባራቸው ከአላህ መራቅን እንጂ ሌላን አይጨምርላቸውም።

በተጨማሪም ይህ ጠቃሚና በቁርኣን እና በሐዲስ ማስረጃዎች ፀድቆ የመጣው የሸፋዓ አይነት ዑለማዎች አላህ ይዘንላቸውና በሁለት እንደሚከፈል ጠቅሰዋል። ጥቅልና ለየት ያሉ። ጥቅል የሆኑ ሲባል አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ)  ለሻው ባሮቹ እንዲያማልዱ የሚፈቅድላቸው አሉ። ለየት ያለው የሸፋዓ አይነት ደግሞ ለነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም )  ብቻ የተሰጠ የሸፋዓ አይነት ነው። ለርሳቸው ቂያማ እለት ከሚሆነው ታላላቅ የሸፋዓ ዓይነት ሰዎች ፀሐይ አናታቸው ላይ ስትሆን ጭንቀትና ሐሳብ ይገባቸዋል።ከዚህ ጭንቅ አላህ እንዲገላግላቸው ሸፋዓ የሚሆንላቸውን ሰው ይፈልጋሉ። ስለዚህም ወደ አደም፣ቀጥሎም ወደ ኑሕ ቀጥሎም ወደ ኢብራሂም፣ቀጥሎም ወደ ሙሳ ቀጥሎም ወደ ኢሳ ይሄዳሉ።ሁላቸውም ማማለድ እንደማይችሉ ይነግሯቸዋል። በስተመጨረሻም ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ጋር ይደርሳሉ፤ እርሳቸውም ተነስተው ወደ ዐርሽ በመሄድ አላህ ባሮችን ከዚህ ጭንቅ  እንዲገላግል ምልጃ ያቀርባሉ። አላህም ልመናቸውን እና ሸፋዓቸውን ይቀበላል። ይህ አላህ ቃል ከገባላቸው ምስጉኑ ስፍራ ላይ መቆም ከሚለው ውስጥ የሚካተት ነው። አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ)  እንዲህ ይላል፦

“ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የሆነችን ሶላት በእርሱ (በቁርኣን) ስገድ፡፡ ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል፡፡” [አል ኢስራእ:79]

 ለረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ብቻ ከተሰጣቸው የሸፋዓ ዓይነቶች መካከል የጀነት ሰዎች ጀነት እንዲገቡ ምልጃ ያደርጋሉ። ይኸውም የጀነት ሰዎች ሲራጥን እንዳለፉ በጀነትና በእሳት መካከል ያለው ድልድይ ላይ ይቆማሉ። በመሃከላቸው ቂም ካለ ከፊላቸው ከከፊሉ ልባቸው ንፁህ ይደረጋል፤ ከፀዱና ከጠሩ በኋላ ጀነት እንዲገቡ ፍቃድ ይሰጣቸዋል።ነገር ግን ጀነትን ያለ ነቢዩ ሸፋዓ ሊገቡ አይችሉም። የጀነት በሮች በነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም )  ሸፋዓ አማካኝነት ይከፈታሉ።

ለነቢዩም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም )  ይሁን ከሳቸው ውጭ ላሉ ደጋግ ባሮች የሚፈቀደው የሸፋዓ አይነት ፦ በወንጀላቸው የተነሳ እሳት የገቡ  ወንጀለኞች፤ እሳት ውስጥ መዘውተር የማይገባቸው አማኞች  ከእሳት እንዲወጡ አማላጅ ይሆኑላቸዋል። ይህ የሸፋዓ አይነት ለመልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ፣ ለሰማዕታት፣ ለደጋግ ባሮች የሚገባ የሸፋዓ አይነት ነው። ወላሁ አዕለም!


 
Share

ወቅታዊ