Back to Top
ከፊርቀቱ ናጂያ ለመካተት እነዚህ አራቱ መገለጫዎች ማለትም ዐቂዳ፣ ዒባዳ፣አኽላቅ እና (ሙአመላ)ማህበራዊ ኖሮ በሙሉ አንዱም ሳይጓደል ማሟላት ግዴታ ነውን? አንድ ሰው ከነዚህ መካከል አንዱ ቢያጓደል ከፊርቀቱ ናጂያ ይወጣል ወይስ አይወጣም?
   ዐቂዳ (እምነት ነክ ጉዳዮች)

አንዳንድ መገለጫዎች መጓደል የሚያሳድረው መጥፎ ተፅእኖ


ጥያቄ(54): ከፊርቀቱ ናጂያ ለመካተት እነዚህ አራቱ መገለጫዎች ማለትም ዐቂዳ፣ ዒባዳ፣አኽላቅ እና (ሙአመላ)ማህበራዊ ኖሮ በሙሉ አንዱም ሳይጓደል ማሟላት ግዴታ ነውን? አንድ ሰው ከነዚህ መካከል አንዱ ቢያጓደል ከፊርቀቱ ናጂያ ይወጣል ወይስ አይወጣም?
መልስ:

ከነዚህ አንዱማጓደል አንድን ሰው ከፊርቀቱ ናጂያ አያስወጣውም። ነገር ግን አላህ እንዳለው ፦

“ለሁሉም ከሠሩት ሥራ (የተበላለጡ) ደረጃዎች አልሏቸው፡፡ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡” [አል አንዐም፡132]

ምናልባት አንድ ሰው ተውሒድን በመጓደሉ ወይም ቢድዓን በመስራቱ የተነሳ ከፊርቀቱ ናጂያ ሊወጣ ይችላል። ለምሳሌ ኢባዳው ላይ ያልታዘዘውን በመጨመር ወይም ኢኽላስ የጎደለውን ዒባዳ ቢሰራ ፤ቢድዓ በመስራትም የተነሳ እንዲሁ ከፊርቀቱ ናጂያ ሊወጣ ይችላል።  ነገር ግን አኽላቅና ማህበራዊ ኑሮ ክፍተት ቢፈጠር ሰውዬው ወንጀለኛ ይሆናል እንጂ ከፊርቀቱ ናጂያ አይወጣም።




Share

ወቅታዊ