ጥያቄ(53): “ፊርቀቱ ናጂያ” ከሌሎች አንጃዎች ለየት የሚያደርጋቸው ዋና ዋና መገለጫዎች ምንድን ናቸው?
መልስ:
“ፊርቀቱ ናጂያ” ከሌሎች አንጃዎች ለየት ከሚያደርጋቸው ጉልህ መገለጫቸው መካከል መልዕክተኛው (صلى الله عليه وسلم ) የነበሩበት ዐቂዳ፣ ዒባዳ፣አኽላቅ እና (ሙአመላ)ማህበራዊ ኖሮን አጥብቆ መያዝ ነው። እነዚህ አራት ነገሮች “ፊርቀቱ ናጂያ” ዎች በግልፅ የሚታወቁባቸው ነገሮች ናቸው።
ዐቂዳን አስመልክቶ፦ ቁርኣንና ሐዲስ ተጠቁመው የመጡት እንደ ሩቡቢያ ኡሉሂያ እና አስማኡ ወሲፋት ያሉ ፍፁም የሆነውን ተውሒድ በደንብ አጥብቀው ይይዛሉ።(1)
ዒባዳን አስመልክቶ ፦ ከሌሎች ፊርቃዎች በተሟላ መልኩ መልክተኛው ይሰሯቸው የነበሩ ዒባዳዎችን በአይነታቸው፣አፈፃፀማቸው፣ቁጥራቸው፣ወቅታቸው፣ቦታቸው እና ሰበባቸው ጠብቀው በመፈፀምና በመተግበር ላይ ለየት ብለው ታገኛቸዋለህ። በዲን ጉዳይ ላይ ቢድዓን ሲፈጥሩ አታገኛቸውም። እንዲያውም ከአላህ እና ከመልክተኛው ጋር እጅግ የላቀ እና ጥግ የደረስ ስርዓት አላቸው። አላህ ያልደነገጋቸውና ያላዘዛቸው ነገሮችን በአምልኮት ላይ በማስገባት ከአላህና ከመልክተኛው ቀደም ቀደም አይሉም።
በተጨማሪም በአኽላቃቸውም ከሌሎች ሰዎች የተለዩ ናቸው፤ስለዚህም ለሙስሊሞች በሙሉ መልካሙን በመውደድ፣ለሁሉም ልብን ሰፊ በማድረግ፣ ፈገግታ በመለገስ፣ማራኪ ቃልን በመጠቀም እና የመሳሰሉትን የላቁ እና ጥሩ ስነ ምግባሮች ላይ ታንፀው ታገኛቸዋለህ። ማህበራዊ ኑሮ ላይም እንዲሁ በእውነተኝነትና ነውርን ሳይደብቁ በግልፁ ከሰዎች በሙሉ ይኗኗራሉ። እነዚህ መገለጫዎችን አስመልክቶ መልክተኛው እንዲህ ይላሉ፦
እነዚህ መለያዎችና ምልክቶች በሙሉ ነቢዩ (صلى الله عليه وسلم ) የነበሩበት አቋምና ተግባር ላይ በመሆን የሚታወቁ “ፊርቀቱ ናጂያ” የሆኑት የአህሉ ሱና መገለጫዎች ናቸው።
(1)፡ በሩቡቢያ፤ በኡሉሂያና በአስማወሲፋት አለህን በብቸኝነት ማጥራትን የመሳሰሉ ቁርዓንና ሐዲስ ያመላከታቸውን ነገራት በሙሉ አጥብቀው ይይዛሉ።