ጥያቄ(5): የመጀመሪያው የምስክር ቃል ሁሉንም የተውሒድ ክፍሎችን ያካትታልን?
መልስ:
አዎን። ሁሉንም የተውሒድ ክፍል ያካትታል። በውስጡ ሲታቀፍ አሊያም በተዘዋዋሪ መልዕክቱ ተውሒድን በውስጡ ያቀፈ ነው። አንድ ሰው ላ ኢላህ ኢለላህ ብሎ ሲመሰክር ወዲያውኑ ወደ አዕምሮው የሚመጣው አምልኮትን ነጥሎ ለአላህ ብቻ ማድረግ የሚለው ግንዛቤ ነው። ተውሒድ አል ዒባዳ ተውሒድ አል ኡሉሂያ ተብሎ የሚሰየም ሲሆን በውስጡ ተውሒድ ሩቡቢያን አቅፎ ይዟል። ምክንያቱም ማንኛውም አላህን በአምልኮት ነጥሎ የሚገዛ አካል መጀመሪያ የአላህን ጌትነት ካላረጋገጠ አላህን በአምልኮ ነጥሎ ሊያመልክ አይችልምና። በተጨማሪም ተውሒዱ አስማኢ ወሲፋትንም በውስጡ አካቶ ይዟል። ምክንያቱም መልካም ስምና የላቁ መገለጫ ያለውንና አምልኮት የሚገባው አካል መሆኑ ካወቀ በኋላ ቢሆን እንጂ አምልኮን የሰው ልጅ አይፈጽምምና።
ለዚህም ነው ኢብራሂም አለይሂሰላም ለአባቱ እንዲህ ያለው፦
ስለዚህም ተውሒዱ አልዒባዳ ማለት ተውሒዱ ኡሉሂያህ ሲሆን በውስጡ ተውሑዱ ሩቡቢያና ተውሒዱ አስማኢ ወሲፋት በውስጡ አካቶ ይዟል።