ጥያቄ(38): ስለ ኮከብ ቆጠራ ስንነጋገር ከድግምት እንደሚቆጠር ጠቅሰውልን ነበር እና ድግምት ምንድን ነው?
መልስ:
ሲሕር(ድግምት) ኡለማዎች እንዳብራሩት ከሆነ ፦ ሰበቡ ስውርና ድብቅ የሆነ ነገር ሲሆን በሰዎች ዓይን የማይታይ ተፅእኖ ድግምት ይባላል። ኮከብ ቆጠራና ጥንቆላ በዚህ ትርጉም ውስጥ ይካተታሉ። እንዲያውም ማራኪ አገላለፅ መጠቀም ድግምት ውስጥ ይካተታል። መልክተኛው እንዳሉት፦ “ከማራኪ አገላለፅ መካከል ሲሕር የሆነ አለ።” ማንኛውም ተፅእኖው ግልፅ ያልሆነና ስውር የሆነ ነገር በሙሉ የድግምት አይነት ነው።